Open top menu
October 17, 2020
የገዳ ሥርዓት [ክፍል ፩]  - ( Achamyeleh Tamiru )

የገዳ ሥርዓት [ክፍል ፩]

( Achamyeleh Tamiru ) -

የኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ዲና [ጠላት] እያሉ ጥላቻ በማስተማር ባሳደጉት የቄሮ ትውልድ ጭካኔና አውሬነት የረኩ አይመስልም። ይህም በመሆኑ አውሬ ካደረጓቸው የኦሮሞ ቄሮዎች አልፈው የአዲስ አበባ ልጆችም ገዳ የሚባለውን ኋላቀር የወረራና ወታደራዊ ሥርዓት እንዲያውቁና ወደ አረመኔነት እንዲመለሱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።

የገዳ ሥርዓት የኦሮሞ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ሲወር ከ28 በላይ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን፣ ነገዶችን፣ ማንነቶችንና ባሕሎችን በተሳከ ሁኔታ ያጠፋበት ወታደራዊ ሥርዓት ነው። የገዳ ሥርዓት በኦነጋውያንና ደቂቆቻቸው እንደሚደሰኮረው እንኳን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሊሆን ቀርቶ የፖለቲካ ስርዓት እንኳን አልነበረም። የገዳ ሥርዓት የአርመኔነት ጥግ የታየበት ወታደራዊ ሥርዓት ነበር። ይህን የምለው ፈጥሬ ሳይሆን ከዋናው የገዳ ታሪክ መዝጋቢ ከአባ ባሕርይ መጽሐፍ በተጨማሪ አባ ባሕርይ የጻፉትን ታሪክ ዝቀው የመመረቂያ ወረቀቶቻቸውን ካሰናዱት ከኦሮሞ ብሔርተኞቹ ከፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ከፕሮፈሰር ሕዝቃኤል ጊቢሳ፣ ከፕሮፌሰር ተሰማ ጠአ፣ ወዘተ ጽሑፎች ሳነብ ያገኘሁትን ታሪክ መሰረት በማድረግ ነው።

የገዳ ሥርዓት ከሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች የሚለየው በምርኮኞች ላይ ሳይቀር ritualized የሆነው culture of violenceን ተቋማዊ ማድረጉ ነው። ሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች ሰላማዊ ሰው አይገድሉም፤ ተፋላሚ ጠላት እንኳ ቢሆን የምርኮ አያያዝ ሥርዓት አላማቸው። የገዳ ሥርዓት ግን ተቀዳሚ ኢላማው የታጠቀ ተፋላሚ ኃይል ሳይሆን አገር አማን ብሎ የተቀመጠ ሰላማዊ ሕዝብ ነው። በገዳ ሥርዓት አንድ ሰው ለግድያ ከመሰማራቱ በፊት ለወኔው ማነሳሻ ብዙ ደም ይጠጣል፡፡ ከዚያም አገር አማን ነው ብሎ የሚሄደን መንገደኛ ወይም በቤቱ የተቀመጠን ሰላማዊ ሰው አድብቶ በመግደል ወንድ ከሆኑ ብልቱን፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ጡቷን ቆርጦ ወደ ጎጆው ይመለሳል፡፡ ሲመለስ ፉከራ ያሰማል፡፡ እንዲሁም ሰልቦ የገደለውን ሰው ያሰማውን የጣእር ድምጽ አስመስሎ በመጮህ ያፌዛል፡፡ አንድ የኦሮሞ ወንድ ይህንን ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው በጆሮው ላይ የብር ሎቲ ማንጠልጠል የሚፈቀድለት ወይም በግንባሩ ላይ ከለቻ የሚያስረው።

በቡታ በዓል ሰው ገድሎ መመለስ ያልቻለ ኦሮሞ ውርደት ይከናነባል፤ በግንባሩ ላይ ምልክት ይደረግበትና ወንድ አለመሆኑ ለማሳየት በትንሽ እቃ ወተት ተሰጥቶት ቅቤ እስኪወጣ ድረስ እንዲገፋው ይደረጋል። አንድ ኦሮሞ ሰው ካልገደለ በቀር በገዳ ሥርዓት ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡ [ Huntigford, G. W. (1955). The Galla of Ethiopia: The kingdoms of Kafa and Janjero, Page 64]

ብቸኛው የገዳ ታሪክ ምንጭ አባ ባሕርይ ምስጋና ይግባቸውና የገዳ ሥርዓትን ከእድሜ ደረጃ አወጣጥ ጀምሮ እያንዳንዱ የሥርዓቱ ደንቦች የተቃኙት ወታደራዊ የበላይነትን ለማስገኘት እንደሆነ አስገንዝበውናል። በገዳ ሥርዓት መሪ ሆኖ የሚመረጠው ሰው ከእድሜ አቻዎቹ ብዙ ሰው የገደለው ነው። ከመመረጡ በፊት ሰውን አድኖ ገድሎ ለመረጃነት ይዞ ያልተገኘ ኦሮሞ በገዳ ሥርዓት አይመረጥም። በገዳ ሥርዓት አንዱ ሉባ ከጓደኞቹ መካከል በልጦ ለመገኘት በተለይ ወንዶችን፣ በእናት ማኅጸን ውስጥ ያለ ሕጻንን ጨምሮ ገድሎ ቸብቸቦውን ይዞ መቅረብ የሥርዓቱ አንድ አካል ነው። ባጭሩ የገዳ ስርዓት የገዳዮች ስርዓት ነው።

የገዳ ሥርዓት ምንም ዓይነት የዲሞክራሲ መልክ እንዳልነበረው የሚያሳየው ሌላው አቋሙ የፖለቲካ ስርዓቱ መሪ (አባ ቦኩ) በቤተሰብ ተወራራሽ ወይም ከልጅ ልጅ የሚያልፍ መሆኑ ነው። እውነተኛው ኦሮሞ ምንም እንኳን በቁጥር ትንሽ[ከአስር እንድ] ቢሆንም ወታደራዊ የበላይነትን እንዲያገኝ ያደረገው ይህ ለጦርነት የሰላው አደረጃጀቱ ግን ቁጥሩ እንዲበዛ አድርጎታል። አባ ቦኩ (የፖለቲካ ቢሮው) ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ በመሆኑ ተቋማዊ ትውፊቱን (institutional memory) ሲያስቀጥል የወታደራዊ ክንፉ የሚሞላው በጉልበትም፣ በእድሜም የመግደል ችሎታቸው ከፍተኛ በሆኑ መሪዎች ነበር። ይህ በሌሎች የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ከነበረው ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ ከሚተላለፈው የስልጣን ሽግግር ሙሉ በሙሉ የተለየ ነበር።

ሞጋሳ የገዳ ሥርዓት ምሰሶ ነው። የሞጋሳ ሥርዓት የተጀመረው እውነተኛ ኦሮሞ የሆኑት የቦረናና ባሬንቱ ነገዶች ወረራ ሲጀምሩ የሚወሩት ግዛት እያሰፋ በመሄዱ ቁጥራቸው ሳስቶ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ነበር። በዚህ ጊዜ የወረሩትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመግደል የማረኩትን ባሪያ፣ ገባርና ገርባ ቢያደጉት የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ተረድተው የመጀመሪያ ልምዳቸውን ሻሽለውታል። በዚህ ጊዜ ነበር የጉዲፈቻና ሞጋሳ ሥርዓቶች በስራ ላይ መዋል የጀመሩት። ቦረናና ባሬንቱ ሲስፋፉ በጦርነት የያዙትን ሕዝብ ገድለው ከመጨረስ ይልቅ ባሕሉንና ቋንቋውን በማጥፋት፣ በምንም ዓይነት ማንነቱን ወደ ኋላ እንዳያስታውስ አድርገው የአባቱን ስም ሳይቀር በመቀየር ለጦርነቱ የሚማገድ ኃይል ለማድረግ ነበር ሞጋሳ የተጀመረው። እንዲህም ከተደረገ በኋላ በሞጋሳ የተያዘው ኦሮሞ አልተደረገም ገርባ እንጂ። ገርባ አገልጋይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞው በፈለገ ጊዜ የሚሸጠው ባሪያም ነበር። ለዚህ ምንጭ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ከሰላሳ ዓመታት በፊት “The Oromo of Ethiopia: A History, 1570-1860” በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 126 ላይ የጻፈውን ያነቧል።

የሞጋሳ ስሪት ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሥርዓት ነበር። በገዳ ሥርዓት መሰረት ገርባ የተደረገው ሕዝብ ማንነቱን እንዲያጣ ተደርጎ፤ ከማኅበራዊ ቦታውም ወጥቶ መሬትም ሆነ ሌላ ንብረት እንዳያፈራ ይከለክላል። ገርባ የኦሮሞ ንብረት ብቻ ነበር። ባጭሩ ገርባ ምንም እንኳን ኦሮምኛ እንዲናገር ቢገደድም ኦሮሞ ግን ፈጽሞ አልነበረም፤ እንዲሆንም የገዳ ሥርዓትም አይፈቅድለትም።

ከ17ኛው እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ድረስ አብዛኛው የባሪያ አቅራቢዎች ሞቲ[የኦሮሞ ንጉሥ] የሆኑት አንጋፋዎች እንደነበሩ የተመዘገበ ታሪክ ነው። በዚህም የተነሳ አብዛኛው ባሪያ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነበር። ይህ ማለት ግን ሞቲዎች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ኦሮሞዎችን ነበር ማለት አይደለም። በሞቲዎችና አባገዳዎች ለሽያጭ የሚቀርቡት አገልጋይ የነበሩ ገርባዎች ነበሩ። በደቡቡ፣ በምዕራቡና በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ከአባገዳ መር የዘር ጀኖሳይድ የተረፉት ነገዶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሞቲ ባሪያ ፈንጋዮች ጥቃትን ያስተናግዱ ነበር። ለዚህ የሚከተሉትን እውነታዎች መጥቀስ ይቻላል።

ዳግማዊ አባ ጅፋርን በ1904 ዓ.ም. በሚኖሩበት ጅማ ሄዶ የጎበኛቸው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም አባ ጅፋር «ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካባቢውን ሕዝብ በተለይም የሞችን በባርነት ሽጦ እንደጨረሰው» ኦቶባዮግራፊ [የሕይወቴ ታሪክ] በሚል ባዘጋጁት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ አስፍረዋል።

Achamyeleh Tamiru, [16.10.20 03:10]
በ1916 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] አባል ለመሆን ባመለከተችበት ወቅት በእንግሊዝ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦባት ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት የአባልነት ማመልከቻ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] ለማስገባት ወደ ጀኔቫ የተላከው ቡድን መሪ የነበሩት ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው «አባ መብረቅ» እንግሊዝ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባል እንዳትሆን የተቃወመችበትን ምክንያት ለንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በላኩት የቴሌግራም መልዕክት፤

«እንግሊዝ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሐን የዘገቡትንና በሱዳን፣ በኬንያ፣ በኤደንና በግብጽ ባሉት የቅኝ ግዛት መንግሥቱ በኩል የሰበሰበውን ማስረጃ በማያያዝ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለነበረው የባርያ ንግድ ሁኔታ፤ በተለይም የጂማው አባ ጅፋር በከፋ፣ በማጂ፣ በጊሚራና በጉራፈርዳ ሕዝብ ላይ እየካሄዱት ያለው መጠነ ሰፊ የባሪያ ንግድ ለማኅበሩ የፖለቲካ ኮሚሲዮንና ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ አባል እንዳንሆን ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርቦብናል»

ሲሉ አስረድተዋል።

ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በአባ ጅፋር አማካኝነት የሚካሄደው የባርያ ንግድ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እንዲታገድና የሰው ልጅ መብት በመላው የአገሪቱ ግዛት እንዲከበር የአልጋወራሽ ተፈሪ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ቃል በመግባት ኢትዮጵያ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከመስከረም 17 ቀን 1916 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ማህበር 57ኛ አባል ሆና መመዝገቧ በይፋ ታወጀላት።

ባጭሩ በአባ ገዳ የተመራው የኦሮሞ ገዢ መደብ ወረራ ተሳክቶለት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠር ኖሮ ሁሉም ባሕልና ቋንቋ ተጨፍልቆና ተሰልቅጦ ዛሬ ሁሉም አንድ ወጥ ኦሮሞ ብቻ ይሆን ነበር። ለዚህ ማሳያው ቀላል ነው። ኦሮሞ በወረራ የያዛቸው የጥንት ነገዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ኦሮሞነት ተቀይረዋል። ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ይኖሩ የነበሩት ጥንታዊ ነገዶች ሁሉ ጸድተው ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል። ይህም የሆነው በዋናነት በገዳ ሥርዓ ነው። እንደ መልካም ነገር የአዲስ አበባ ልጆች እንዲማሩት እየተፈለገ ያለው ይህንን ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገዶች የጸዱበትን ሥርዓት ነው።

ገራሚው ነገር ዛሬ ገዳን ለሌላው ሊያስተምሩ የተነሱት ባለጊዜዎች «ተበደልን፣ የዘር ጥቃት ደረሰብን» ብለው ሊያለቃቅሱ የነበሩና በጦረኛ አባገዳዎች ተሸንፈው የተያዙ ገርባ ልጆች መሆናቸው ነው። እነዚህ ገርባዎች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ተነስተው አባ ላፋዎች [የኦሮሞ የመሬት ከበርቴዎች]፣ ሞቲዎች፣ መልከኞች [የአካባቢ ገዢዎች]፣ አባ ገዳዎች ወዘተ ጠቅልለው ከያዙት መሬት ውስጥ ቀንሰው የሚያርሱት መሬትና የግል ንብረት ባለቤት እስኪያደርጓቸው ድረስ መሬትም ንብረትም እንዳልነበራቸው አያውቁም። ይህን ባለማወቃቸው ዛሬ በኦነጋውያን በየአካባቢው የሚደርሰውን ጥቃትና ተዳፍኖ የቆየው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በሞጋሳ የጠፉበት የገዳ ሥርዓት የወለደውን ጦረኝነት ክፍል ሁለት ለማስቀጠም ገዳን ሊያስተምሩ ይዳዳቸዋል።

ኢትዮጵያ የተወረረችበትን፣ ነባር ነገዶቿ ከርስታቸው የፈለሱበትን፣ 400 ዓመታት ሙሉ በደም ጎርፍ የታጠብንበትን፣ ከ28 በላይ የኢትዮጵያ የጥንት ነገዶች ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የጠፉበትን የገዳን ሥርዓት ከጥፋቱ ለተረፉት ማስተማር ስድስት ሚልዮን አይሁዶችን ለጥፋት የዳረገውን የናዚ ሥርዓት ለእብራውያን ልጆች ከማስተማር ተለይቶ አይታይም። የናዚዎቹን ስኬት ለማስተማር የሚፈልጉ የሉም ማለት አይደለም። በደንብ አሉ። ሆኖም ግን ታሪክ በትክክል በመነገሩ ጨካኝ የናዚ ሥርዓት በዓለም ላይ እየተወገዘ እንዲኖርና ተመልሶ እንዳይመጣ ተደርጓል። በአገራችን ግን ታሪካችንን በደምብ ባለማወቃችን፣ የዘር ማጥፋትን የተካሄደበትና ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች የጠፉበትን ገዳን እንደበረከት እንድንማረው እየተደረግን እንገኛለን። ታሪካችንን ጠንቅቀን ያወቅን ቢሆን ኖሮ የጠፋንበትን ወታደራዊና የወረራ ሥርዓታቸውን እንድንማር ሳይሆን በወረራ በያዙት ባድማ ላይ የነባሩን ሕዝብ ቋንቋ፣ ባሕልና ሃይማኖት አጥፍተው የሰፈሩት የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት አባገዳዎች ቋንቋና ባሕላቸውን ላጠፉባቸው፣ መሬታቸውን ነጥቀው ገርባ ላደረጓቸው፣ ባሪያ አደርገው ለሸጧቸው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ እንችል ነበር።

Achamyeleh Tamiru, [16.10.20 03:16]
[ Photo ]

Achamyeleh Tamiru, [16.10.20 13:33]
ኦሮሞን ባርያ አድርጎ የሸጠው ባርያ ፈንጋይ ማን ነበር?

የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን በጃዋር መሐመድ ቴሌቭዥን ቀርቦ “በዲሞክራሲያዊነቱ ወደር የለውም በሚሉት የገዳ ሥርዓት ላይ በመሰንዘር ላይ የሚገኙ ጥቃቶች” ያላቸውን ትችቶች ለመከላከል ሞክሯል። ሆኖም ግን በዘመኑ በተመዘገበ፤ በቀዳሚ የታሪክ ማስረጃ ላይ ተመስርተን የዘር ማጥፋትና የወረራ ወታደራዊ ሥርዓት ስለሆነው ስለ ገዳ የሰነዘርነውን ትችት እንደ ታሪክ ባለሞያ እንዱንም እንኳ በማስረጃ ላይ ተመስርቶ ሳይከላከል እሱና ሌሎች የኦሮሞ ብሔርተኞች ስለ ገዳ ድርጅት የፈጠሩትን ፕሮፓጋንዳ ብቻ አስተጋብቶ ከቴሌቭዥኑ መስኮት ወርዷል።

አስተርጉሜ በሰማሁት ዲስኩሩ ውስጥ ያስተጋባው አንዱ የፈጠራ ትርክቱ ግን ሳያስገርመኝ አልቀረም። የገዳ ድርጅትን እውነተኛ ታሪክ የምናቀርብ ሰዎችን “ኦሮሞን ባርያ አድርገው ይሸጡ የነበሩ ነፍጠኛ ልጆች በሰዎች እኩልነት የሚያምነውን የገዳ ሥርዓት የባርያ አሳዳሪዎች ሥርዓት አድርገው የመተቸት የሞራል ልዕልና የላቸውም” ሲል ደፋር ንግግር አድርጓል። ይገርማል! ጤና ይስጥልኝ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን ማነው ኦሮሞን ባርያ አድርጎ የሸጠው? እስቲ ዶሴው ይውጣና ይመርመር።

ኦሮሞን ፈንግሎ ማን ባርያ አድርጎ እንደሸጠው የሚያሳይ የታሪክ ማስረጃ ስናፈላልግ ፕሮፈሰር ሳንድራ ሼል የተባሉ የታሪክ ምሑር “Children of Hope፡ The Odyssey of the Oromo Slaves from Ethiopia to South Africa በሚል በቅርቡ ያሳተሙትን ጥናት እናገኛለን።

ከታች የታተሙት ሁለት ጥናታዊ መግለጫዎች ዛሬ ኦሮምያ ክልል ከሚባለ አካባቢ በባርያ ነጋዴዎች ተፈንግለው ወደ ደቡብ አፍሪካ የተሸጡ የኦሮሞ ልጆችን ማን ፈንግሎ እንደሸጣቸው የሚያሳዩ የፕሮፈሰር ሳንድራ ሼል ጥናት ውጤቶች ናቸው። ወደ ደቡብ አፍሪካ የተሸጡ የኦሮሞ ልጆችን ማን ፈንግሎ እንደሸጣቸው የሚያሳየው ይህ የፕሮፈሰር ሳንድራ ሼል የጥናት ውጤት የሚገኘው ፕሮፈሰሯ “Children of Hope፡ The Odyssey of the Oromo Slaves from Ethiopia to South Africa” በሚል ርዕስ አዘጋጅተው በኦሀዮ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ከገጽ 65 እና 66 ነው። ፕሮፈሰር ሳንድራ የኦሮሞ ልጆችን ማን ፈንግሎ እንደሸጣቸው ያጠኑት ተፈንጋዮቹ የኦሮሞ ልጆች ራሳቸው ከሰጡት የራስ ምስክር ነው። ጥናቱ የሚያጠቃልለው እስከ 1882 ዓ.ም. ድረስ የተፈነገሉትን በመቶዎች የሚዎጠሩ የኦሮሞ ወንድና ሴት ልጆችን ነው።

ከታች በታተመው ጥናት መሰረት 35 ፐርሰንቱ የኦሮሞ ልጆች በኦሮሞ ተወላጆች እንደተፈነገሉና ባርያ ተደርገው እንደተሸጡ ተናግረዋል። 23 ፐርሰንቱ ደግሞ በሲዳማ ተወላጅ ፈንጋዮች እንደተሸጡ ቃላቸውን ሰጥተዋል። የተቀሩት ተፈንጋዮች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ነገዶች በተወለዱ ባርያ ነጋዴዎች እንደተፈነገሉ ተናግረዋል።

በጥናቱ የተካተቱ በባሪያ ነጋዴዎች የተፈነገሉ የኦሮሞ ሁሉ በሰጡት የቃል መሰረት ግን አንድም የአማራ ተወላጅ የሆነ ሰው በመፈንገል ባርያ አድርጎ እንደሸጣቸው የሚያሳይና ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል የአንድም ተፈንጋይ እንኳን የቃል ምስክር የለም። ተፈንጋዮቹ የኦሮሞ ልጆች ራሳቸው በሰጡት የቃል ምስክር ባብዛኛው የፈነገላቸው የኦሮሞ ተወላጅ ባርያ ነጋዴ መሆኑን በተናገሩበት ሁኔታ፤ አንድም የአማራ ተወላጅ ፈንግሎ እንደሸጠ እንዳቸውም ተፈንጋዮች ባልተናገሩበት ሁኔታ ነው እንግዲህ “የታሪክ ምሑሩ” ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ያለ አንዳች ማስረጃ በጥላቻና በጨበጣ አማራን በባሪያ ሻጭነት የሚከሰው። በታሪክ ተመዝግቦ የምናገኘው እውነትና ተፈንጋዮቹ የኦሮሞ ልጆች ራሳቸው በሰጡት የታሪክ ምስክር መሰረት ግን ኦሮሞን ፈንግሎ ባርያ አድርገው የሸጠው ጎረቤቱ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ ማርያ ፈንጋይ መሆናቸው ነው።

ፕሮፈሰር ሳንድራ ሼል በጥናታቸው የሚነግሩን ሌላም አስዳማሚ የታሪክ እውነት አለ። የኦሮሞ ተወላጅ ባርያ ፈንጋዮች ባሪያ አድርገው የሸጧቸውን የአሮሞ ልጆች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመላላክ ገንዘብ ጭምር እየከፈሉ ነጻ እንዲወጡና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ይነግሩናል። ከነዚህ በኦሮሞ ተወላጆች ወደ ደቡብ አፍሪካ ከተሸጡት ባሮች መካከልም ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ገንዘብ ከፍለው ነጻ ያወጡት ያንዱ ሰው ትውልዶች በማውሳት በደርግ ዘመን ከኢትዮጵያ ወደ ካናዳ ተሰደው አሁንም ድረስ ካናዳ ውስጥ እንደሚኖሩ ነግረውናል። የተዘመገው የታሪክ እውነት ይህ ሆኖ ሳለ ነው እንግዲህ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ሳያፍር የኦሮሞ ተወላጆች የሰጧቸውን የኦሮሞ ባሮች ገንዘብ ከፍለው ነጻ ያወጧቸውን የዐፄ ምኒልክ ልጆች “ኦሮሞን ባርያ አድርገው ይሸጡ የነበሩ ነፍጠኛ ልጆች የገዳ ሥርዓትን የባርያ አሳዳሪዎች ሥርዓት አድርገው የመተቸት የሞራል ልዕልና የላቸውም” የሚለው።

በስተመጨረሻም ሳይመረምሩ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ያራገፉባቸውን የአህይነት ጭነት ተሸክመው እየዞሩ አማራን በባርያ ፈንጋይነት የሚከሱ የኦሮሞ ብሔርተኞችንና ደጋሚዎቻቸውን «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት» የሚለውን የአያቶቻችን ጥልቅ ምክርና ታላቁ ጥላሁን ገሰሰ «አመልካች ጣት» በሚል በተጫወተው ዘፈን ውስጥ፤

ባንዷ ስትጠቁም ከጣቶችህ መሀል፣
ሶስቱ ግን ራስህን ይመለከቱሀል፤
በሚል ያቀነቀነውን ግጥም በመለገስ ልሰናበት!
_____
ከስር የታተመውን Oromo Man with Berta Slave የሚል መግለጫ ያለውን ታሪካዊ ፎቶ የገኘሁት ወለጋ ውስጥ ወንጌል ሲስብክ የኖረው ወንጌላዊው John G. Hall "Ethiopia in the Modern World (Explorations of Africa)" በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በ2002 ካሳተመው መጽሐፍ ከገጽ 50 ላይ ነው። ሁለተኛው ፎቶ በጀርመንኛ የተጻፈው መግለጫ ያለው ሲሆን መግለጫው ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጎም Galla Man with Sidama slave የሚል ይሆናል።

Read more
የገዳ ሥርዓት [ክፍል ፩]  ( Achamyeleh Tamiru )

የገዳ ሥርዓት [ክፍል ፩]

( Achamyeleh Tamiru ) -

የኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ዲና [ጠላት] እያሉ ጥላቻ በማስተማር ባሳደጉት የቄሮ ትውልድ ጭካኔና አውሬነት የረኩ አይመስልም። ይህም በመሆኑ አውሬ ካደረጓቸው የኦሮሞ ቄሮዎች አልፈው የአዲስ አበባ ልጆችም ገዳ የሚባለውን ኋላቀር የወረራና ወታደራዊ ሥርዓት እንዲያውቁና ወደ አረመኔነት እንዲመለሱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።

የገዳ ሥርዓት የኦሮሞ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ሲወር ከ28 በላይ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን፣ ነገዶችን፣ ማንነቶችንና ባሕሎችን በተሳከ ሁኔታ ያጠፋበት ወታደራዊ ሥርዓት ነው። የገዳ ሥርዓት በኦነጋውያንና ደቂቆቻቸው እንደሚደሰኮረው እንኳን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሊሆን ቀርቶ የፖለቲካ ስርዓት እንኳን አልነበረም። የገዳ ሥርዓት የአርመኔነት ጥግ የታየበት ወታደራዊ ሥርዓት ነበር። ይህን የምለው ፈጥሬ ሳይሆን ከዋናው የገዳ ታሪክ መዝጋቢ ከአባ ባሕርይ መጽሐፍ በተጨማሪ አባ ባሕርይ የጻፉትን ታሪክ ዝቀው የመመረቂያ ወረቀቶቻቸውን ካሰናዱት ከኦሮሞ ብሔርተኞቹ ከፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ከፕሮፈሰር ሕዝቃኤል ጊቢሳ፣ ከፕሮፌሰር ተሰማ ጠአ፣ ወዘተ ጽሑፎች ሳነብ ያገኘሁትን ታሪክ መሰረት በማድረግ ነው።

የገዳ ሥርዓት ከሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች የሚለየው በምርኮኞች ላይ ሳይቀር ritualized የሆነው culture of violenceን ተቋማዊ ማድረጉ ነው። ሌሎች ወታደራዊ ሥርዓቶች ሰላማዊ ሰው አይገድሉም፤ ተፋላሚ ጠላት እንኳ ቢሆን የምርኮ አያያዝ ሥርዓት አላማቸው። የገዳ ሥርዓት ግን ተቀዳሚ ኢላማው የታጠቀ ተፋላሚ ኃይል ሳይሆን አገር አማን ብሎ የተቀመጠ ሰላማዊ ሕዝብ ነው። በገዳ ሥርዓት አንድ ሰው ለግድያ ከመሰማራቱ በፊት ለወኔው ማነሳሻ ብዙ ደም ይጠጣል፡፡ ከዚያም አገር አማን ነው ብሎ የሚሄደን መንገደኛ ወይም በቤቱ የተቀመጠን ሰላማዊ ሰው አድብቶ በመግደል ወንድ ከሆኑ ብልቱን፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ጡቷን ቆርጦ ወደ ጎጆው ይመለሳል፡፡ ሲመለስ ፉከራ ያሰማል፡፡ እንዲሁም ሰልቦ የገደለውን ሰው ያሰማውን የጣእር ድምጽ አስመስሎ በመጮህ ያፌዛል፡፡ አንድ የኦሮሞ ወንድ ይህንን ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው በጆሮው ላይ የብር ሎቲ ማንጠልጠል የሚፈቀድለት ወይም በግንባሩ ላይ ከለቻ የሚያስረው።

በቡታ በዓል ሰው ገድሎ መመለስ ያልቻለ ኦሮሞ ውርደት ይከናነባል፤ በግንባሩ ላይ ምልክት ይደረግበትና ወንድ አለመሆኑ ለማሳየት በትንሽ እቃ ወተት ተሰጥቶት ቅቤ እስኪወጣ ድረስ እንዲገፋው ይደረጋል። አንድ ኦሮሞ ሰው ካልገደለ በቀር በገዳ ሥርዓት ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡ [ Huntigford, G. W. (1955). The Galla of Ethiopia: The kingdoms of Kafa and Janjero, Page 64]

ብቸኛው የገዳ ታሪክ ምንጭ አባ ባሕርይ ምስጋና ይግባቸውና የገዳ ሥርዓትን ከእድሜ ደረጃ አወጣጥ ጀምሮ እያንዳንዱ የሥርዓቱ ደንቦች የተቃኙት ወታደራዊ የበላይነትን ለማስገኘት እንደሆነ አስገንዝበውናል። በገዳ ሥርዓት መሪ ሆኖ የሚመረጠው ሰው ከእድሜ አቻዎቹ ብዙ ሰው የገደለው ነው። ከመመረጡ በፊት ሰውን አድኖ ገድሎ ለመረጃነት ይዞ ያልተገኘ ኦሮሞ በገዳ ሥርዓት አይመረጥም። በገዳ ሥርዓት አንዱ ሉባ ከጓደኞቹ መካከል በልጦ ለመገኘት በተለይ ወንዶችን፣ በእናት ማኅጸን ውስጥ ያለ ሕጻንን ጨምሮ ገድሎ ቸብቸቦውን ይዞ መቅረብ የሥርዓቱ አንድ አካል ነው። ባጭሩ የገዳ ስርዓት የገዳዮች ስርዓት ነው።

የገዳ ሥርዓት ምንም ዓይነት የዲሞክራሲ መልክ እንዳልነበረው የሚያሳየው ሌላው አቋሙ የፖለቲካ ስርዓቱ መሪ (አባ ቦኩ) በቤተሰብ ተወራራሽ ወይም ከልጅ ልጅ የሚያልፍ መሆኑ ነው። እውነተኛው ኦሮሞ ምንም እንኳን በቁጥር ትንሽ[ከአስር እንድ] ቢሆንም ወታደራዊ የበላይነትን እንዲያገኝ ያደረገው ይህ ለጦርነት የሰላው አደረጃጀቱ ግን ቁጥሩ እንዲበዛ አድርጎታል። አባ ቦኩ (የፖለቲካ ቢሮው) ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ በመሆኑ ተቋማዊ ትውፊቱን (institutional memory) ሲያስቀጥል የወታደራዊ ክንፉ የሚሞላው በጉልበትም፣ በእድሜም የመግደል ችሎታቸው ከፍተኛ በሆኑ መሪዎች ነበር። ይህ በሌሎች የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ከነበረው ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ ከሚተላለፈው የስልጣን ሽግግር ሙሉ በሙሉ የተለየ ነበር።

ሞጋሳ የገዳ ሥርዓት ምሰሶ ነው። የሞጋሳ ሥርዓት የተጀመረው እውነተኛ ኦሮሞ የሆኑት የቦረናና ባሬንቱ ነገዶች ወረራ ሲጀምሩ የሚወሩት ግዛት እያሰፋ በመሄዱ ቁጥራቸው ሳስቶ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ነበር። በዚህ ጊዜ የወረሩትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመግደል የማረኩትን ባሪያ፣ ገባርና ገርባ ቢያደጉት የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ተረድተው የመጀመሪያ ልምዳቸውን ሻሽለውታል። በዚህ ጊዜ ነበር የጉዲፈቻና ሞጋሳ ሥርዓቶች በስራ ላይ መዋል የጀመሩት። ቦረናና ባሬንቱ ሲስፋፉ በጦርነት የያዙትን ሕዝብ ገድለው ከመጨረስ ይልቅ ባሕሉንና ቋንቋውን በማጥፋት፣ በምንም ዓይነት ማንነቱን ወደ ኋላ እንዳያስታውስ አድርገው የአባቱን ስም ሳይቀር በመቀየር ለጦርነቱ የሚማገድ ኃይል ለማድረግ ነበር ሞጋሳ የተጀመረው። እንዲህም ከተደረገ በኋላ በሞጋሳ የተያዘው ኦሮሞ አልተደረገም ገርባ እንጂ። ገርባ አገልጋይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞው በፈለገ ጊዜ የሚሸጠው ባሪያም ነበር። ለዚህ ምንጭ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን ከሰላሳ ዓመታት በፊት “The Oromo of Ethiopia: A History, 1570-1860” በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 126 ላይ የጻፈውን ያነቧል።

የሞጋሳ ስሪት ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሥርዓት ነበር። በገዳ ሥርዓት መሰረት ገርባ የተደረገው ሕዝብ ማንነቱን እንዲያጣ ተደርጎ፤ ከማኅበራዊ ቦታውም ወጥቶ መሬትም ሆነ ሌላ ንብረት እንዳያፈራ ይከለክላል። ገርባ የኦሮሞ ንብረት ብቻ ነበር። ባጭሩ ገርባ ምንም እንኳን ኦሮምኛ እንዲናገር ቢገደድም ኦሮሞ ግን ፈጽሞ አልነበረም፤ እንዲሆንም የገዳ ሥርዓትም አይፈቅድለትም።

ከ17ኛው እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ድረስ አብዛኛው የባሪያ አቅራቢዎች ሞቲ[የኦሮሞ ንጉሥ] የሆኑት አንጋፋዎች እንደነበሩ የተመዘገበ ታሪክ ነው። በዚህም የተነሳ አብዛኛው ባሪያ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነበር። ይህ ማለት ግን ሞቲዎች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ኦሮሞዎችን ነበር ማለት አይደለም። በሞቲዎችና አባገዳዎች ለሽያጭ የሚቀርቡት አገልጋይ የነበሩ ገርባዎች ነበሩ። በደቡቡ፣ በምዕራቡና በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ከአባገዳ መር የዘር ጀኖሳይድ የተረፉት ነገዶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሞቲ ባሪያ ፈንጋዮች ጥቃትን ያስተናግዱ ነበር። ለዚህ የሚከተሉትን እውነታዎች መጥቀስ ይቻላል።

ዳግማዊ አባ ጅፋርን በ1904 ዓ.ም. በሚኖሩበት ጅማ ሄዶ የጎበኛቸው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም አባ ጅፋር «ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካባቢውን ሕዝብ በተለይም የሞችን በባርነት ሽጦ እንደጨረሰው» ኦቶባዮግራፊ [የሕይወቴ ታሪክ] በሚል ባዘጋጁት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ አስፍረዋል።

Achamyeleh Tamiru, [16.10.20 03:10]
በ1916 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] አባል ለመሆን ባመለከተችበት ወቅት በእንግሊዝ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦባት ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት የአባልነት ማመልከቻ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] ለማስገባት ወደ ጀኔቫ የተላከው ቡድን መሪ የነበሩት ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው «አባ መብረቅ» እንግሊዝ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባል እንዳትሆን የተቃወመችበትን ምክንያት ለንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በላኩት የቴሌግራም መልዕክት፤

«እንግሊዝ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሐን የዘገቡትንና በሱዳን፣ በኬንያ፣ በኤደንና በግብጽ ባሉት የቅኝ ግዛት መንግሥቱ በኩል የሰበሰበውን ማስረጃ በማያያዝ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለነበረው የባርያ ንግድ ሁኔታ፤ በተለይም የጂማው አባ ጅፋር በከፋ፣ በማጂ፣ በጊሚራና በጉራፈርዳ ሕዝብ ላይ እየካሄዱት ያለው መጠነ ሰፊ የባሪያ ንግድ ለማኅበሩ የፖለቲካ ኮሚሲዮንና ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ አባል እንዳንሆን ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርቦብናል»

ሲሉ አስረድተዋል።

ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በአባ ጅፋር አማካኝነት የሚካሄደው የባርያ ንግድ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እንዲታገድና የሰው ልጅ መብት በመላው የአገሪቱ ግዛት እንዲከበር የአልጋወራሽ ተፈሪ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ቃል በመግባት ኢትዮጵያ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከመስከረም 17 ቀን 1916 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ማህበር 57ኛ አባል ሆና መመዝገቧ በይፋ ታወጀላት።

ባጭሩ በአባ ገዳ የተመራው የኦሮሞ ገዢ መደብ ወረራ ተሳክቶለት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠር ኖሮ ሁሉም ባሕልና ቋንቋ ተጨፍልቆና ተሰልቅጦ ዛሬ ሁሉም አንድ ወጥ ኦሮሞ ብቻ ይሆን ነበር። ለዚህ ማሳያው ቀላል ነው። ኦሮሞ በወረራ የያዛቸው የጥንት ነገዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ኦሮሞነት ተቀይረዋል። ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ይኖሩ የነበሩት ጥንታዊ ነገዶች ሁሉ ጸድተው ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል። ይህም የሆነው በዋናነት በገዳ ሥርዓ ነው። እንደ መልካም ነገር የአዲስ አበባ ልጆች እንዲማሩት እየተፈለገ ያለው ይህንን ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገዶች የጸዱበትን ሥርዓት ነው።

ገራሚው ነገር ዛሬ ገዳን ለሌላው ሊያስተምሩ የተነሱት ባለጊዜዎች «ተበደልን፣ የዘር ጥቃት ደረሰብን» ብለው ሊያለቃቅሱ የነበሩና በጦረኛ አባገዳዎች ተሸንፈው የተያዙ ገርባ ልጆች መሆናቸው ነው። እነዚህ ገርባዎች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ተነስተው አባ ላፋዎች [የኦሮሞ የመሬት ከበርቴዎች]፣ ሞቲዎች፣ መልከኞች [የአካባቢ ገዢዎች]፣ አባ ገዳዎች ወዘተ ጠቅልለው ከያዙት መሬት ውስጥ ቀንሰው የሚያርሱት መሬትና የግል ንብረት ባለቤት እስኪያደርጓቸው ድረስ መሬትም ንብረትም እንዳልነበራቸው አያውቁም። ይህን ባለማወቃቸው ዛሬ በኦነጋውያን በየአካባቢው የሚደርሰውን ጥቃትና ተዳፍኖ የቆየው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በሞጋሳ የጠፉበት የገዳ ሥርዓት የወለደውን ጦረኝነት ክፍል ሁለት ለማስቀጠም ገዳን ሊያስተምሩ ይዳዳቸዋል።

ኢትዮጵያ የተወረረችበትን፣ ነባር ነገዶቿ ከርስታቸው የፈለሱበትን፣ 400 ዓመታት ሙሉ በደም ጎርፍ የታጠብንበትን፣ ከ28 በላይ የኢትዮጵያ የጥንት ነገዶች ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ የጠፉበትን የገዳን ሥርዓት ከጥፋቱ ለተረፉት ማስተማር ስድስት ሚልዮን አይሁዶችን ለጥፋት የዳረገውን የናዚ ሥርዓት ለእብራውያን ልጆች ከማስተማር ተለይቶ አይታይም። የናዚዎቹን ስኬት ለማስተማር የሚፈልጉ የሉም ማለት አይደለም። በደንብ አሉ። ሆኖም ግን ታሪክ በትክክል በመነገሩ ጨካኝ የናዚ ሥርዓት በዓለም ላይ እየተወገዘ እንዲኖርና ተመልሶ እንዳይመጣ ተደርጓል። በአገራችን ግን ታሪካችንን በደምብ ባለማወቃችን፣ የዘር ማጥፋትን የተካሄደበትና ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች የጠፉበትን ገዳን እንደበረከት እንድንማረው እየተደረግን እንገኛለን። ታሪካችንን ጠንቅቀን ያወቅን ቢሆን ኖሮ የጠፋንበትን ወታደራዊና የወረራ ሥርዓታቸውን እንድንማር ሳይሆን በወረራ በያዙት ባድማ ላይ የነባሩን ሕዝብ ቋንቋ፣ ባሕልና ሃይማኖት አጥፍተው የሰፈሩት የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት አባገዳዎች ቋንቋና ባሕላቸውን ላጠፉባቸው፣ መሬታቸውን ነጥቀው ገርባ ላደረጓቸው፣ ባሪያ አደርገው ለሸጧቸው ከሀያ ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ እንችል ነበር። 

Read more
no image

 ገዳና እሬቻ

( በአቻምየለህ ታምሩ ) -
 
ዐቢይ አሕመድና የዘረጋው የአፓርታይድ አገዛዝ ባላደራዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም። የከተማ አስተዳደሩን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቄሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን "ሸገርን ለማስዋብ" በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ አማሮች ናቸው] አምስት አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ባስቋረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከበር አዳነች አበቤ በዐቢይ አሕመድ በተሾመች ሳምንት ሳይሞላት አባገዳ ለሚባሉቱ የይዞታ ካርታ ሰጥታለች።
 
ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባን ይፋዊ ስም ወደ ሸገር ቀይሮ “ሸገርን ማስዋብ” የሚል የማፈናቀያና የጥንቱን የአዲስ አበባ ኗሪ የማጽጃ ፕሮጀክት የቀረጸው የሁላችንም የሆነችን አዲስ ስበባን ለማስዋብ ሳይሆን የኦሮሙማዋን ፊንፊኔ ለመፍጠር ነው። አዲስ አበባ ውስጥ ዐቢይ ባቋረው ሰው ሰራሽ ኩሬ እንዲከበር ቋሚ የይዞታ ካርታ የተሰጠው እሬቻ ዐቢይ አሕመድ "ሸገርን ማስዋብ" የሚል የዳቦ ስም ሰጥቶ እየፈጠራት ላለቸው የኦሮሙማዋ ፊንፊኔ አንድ ማሳያ ነው። ዐቢይ አሕመድም ሆነ ወራሪዎቹ አባገዳዎች አዲስ አበባ ውስጥ ተከብሮ የማያውቀውን እሬቻን አዲስ አበባ ለማክበር ሽርጉድ እያሉ ያሉት የበዓሉ ፍቅር ፈጥርቋቸው ሳይሆን አዲስ አበባ በመውረር የኦሮሞማዋን ፊንፊኔ ለመመስረት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከ150 ዓመት በፊት እዚህ ነበርን ብለው ለፈጠሩት ተረት እንድ "ማስረጃ" የኦሮሞ ባሕል አድርገው የሚያቀርቡትን እሬቻን አዲስ አበባ ውስጥ እንደነበር አድርገው ማቅረብ የግድ ስለሚያስፈልጋቸው ነው።
 
ከዚህ ውጭ አዲስ አበባ ውስጥ ተከብሮ የማያውቀውን እሬቻን አዲስ አበባ ውስጥ ለማክበር የሚነሱበት አንዳች ምድራዊ ምክንያት የለም። ሆኖም ግን እሬቻም ልክ እንደ ገዳ ሁሉ በታሪክ የኦሮሞ አይደሉም። ኦሮሞ ገዳን የተማረው ከባንቱ ነው። የከባንቱ ሥርዓት የነበረውን ገዳን የወረሰውም ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ነበር። ስለዚህ የገዳ ሥርዓት የኦሮሞ ሥርዓት ተብሎ በዩኔስኮ ሊመዘገብ ከቶ አይቻለውም። ገዳ እንደ ሥርዓት በዩኔስኮ መመዝገብ ካለበት የኦሮሞ ተብሎ ሳይሆን የባለቤቶቹ የባንቱዎች ተብሎ ነው። ገዳ የኦሮሞ ሥርዓት እንዳልነበር፤ ኦሮሞ ገዳን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከባንቱ እንደተማረው ታሪኩን አጣርቶ የነገረን ከአባ ባሕርይ ቀጥሎ በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ቀዳሚ ተጠቃሽ የሆነው ጣሊያናዊው ምሑር ፕሮፈሰር ኢኔርኮ ቸሩሊ ነው።

 ፕሮፈሰር ኢኔሪኮ ቸሩሊ ስለ አካባቢው ታሪክ የተጻፈውን የጥንቱን የዜንጅ መጽሐፍ ዋቢ በማድረግ እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. Somalia: Scritti Vari editi ed Inediti I እና እ.ኤ.አ. በ1959 ዓ.ም. Somalia: Scritti Vari editi ed Inediti II በሚል በጣሊያንኛ ቋንቋ ባሳተማቸው መጽሐፍቱ የመዛገበውን ታሪክ ጠቅሶ ጂን ዶሬስ እ.ኤ.አ. በ1971 ዓ.ም. “ Histoire Sommaire de la Corne Orientale de l'Afrique” በሚል ርዕስ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ባሳተመው መጽሐፉ ላይ ታሪኩን እንዲህ ያስቀምጠዋል፤
 
“ዛሬ ሱማሊያ በሚባለው ምድር ሱማሌ ጋላን ተካ። መጀርቲን በሚባለው አካባቢ አንድ መዘክር ወይም የጥንት መጽሐፍ ይገኛል። ይህም ሰነድ ዑባያ በተባለ አካባቢ በሱማሊኛ Galka’yo (ጋል ካ አዮ) የተባለ ቦታ እንዳለ ይጠቅሳል። የቦታው ትርጉም “ጋሎች የለቀቁት [ቦታ] ማለት ነው።. . . ከሰሜን ምስራቅ የመጣው የጋላ ሕዝብ ከመቶ ዓመት በላይ ከዘለቀ ትግል በኋላ ባንቱን ከማዕከላዊ ሶማሊያ አስወጣ፤ [ጋላ] የገዳ ሥርዓትን የወረሰውም ከባንቱ ነው። [በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን] ሱማሌ ጋላን ወግቶ ከሲማሊያ አስወጣ። ጋላ በገዳ ሥርዓት በመጠቀም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ከፍተኛ ለምለም መሬቶች ወረረ” [1]
 
ይህ የቼሩሊ ጥናት በግልጽ እንደሚያሳየው ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን የወረሰው ከባንቱ ሲሆን ሥርዓቱንም ከባንቱ የተዋሰው ኢትዮጵያን ለመውረር ነበር።
 
እሬቻም የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ምድር ሳይስፋፋ መስከረም በገባ መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረው ደብረ ዘይት የአቡዬ የጸበል ሥፍራ በነበረው በሆራ ሐይቅ ነበር። እሬቻ ቃሉ ጭምር የአማርኛ ቃል እንጂ የኦሮምኛ ቃል አይደለም። እሬቻ ኦሮምኛ ነው የሚል ቢኖር የቃሉን የኦሮምኛ ግንድና ቃሉ በኦሮምኛ እንዴት አንደሚረባ ማስረዳት ይጠበቅበታል። የግዕዙ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ "ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት" በሚል ባሰናዱት መዝገበ ቃላት ውስጥ እንደጻፉት እሬቻ ዋናው ሰብል ደርቆ ከመታጨዱና በአውድማ ተወቅቶ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ የደረሰው ተቆርጦ በበትር በመወቃት ወይም በእጅ ታሽቶ የሚቀመሰው እህል ይሉታል። ለላው ሊቅ ከሣቴ ብርሃን ተሰማም በ1951 ዓ.ም ባሳተሙት "የአማርኛ መዝገበ ቃላት" መጽሐፋቸው የአማርኛ ቃል ስለሆነው እሬቻ የሚነግሩን ትርጉም ተመሳሳይ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ1993 ዓ.ም. ባሳተመው “የኣማርኛ መዝገበ ቃላት” ገጽ 101 ላይ እሬቻ የአማርኛ ቃል መሆኑን በመበየን ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጠዋል። ታዋቂው አሜሪካዊ የኢትዮጵያ ታሪክ አጥኚ ቶማስ ኬንም ባዘጋጀው የአማርኛ - እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ቅጽ አንድ ገጽ 397 ላይ ስለ እሬቻ የአማርኛ ቃልነትና ትርጉም የሚነግረን ተመሳሳይ ነው።
 
በመሆኑም የእሬቻ በዓልን የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። ባጭሩ የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።

 የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነገሶ ጊዳዳ፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ አቶ ይልማ ደረሳ፤ ፕሮፈሰር ተሰማ ታዓ፤ ወዘተ እንደነገሩን ደግሞ ኦሮሞ ከብት በማርባት የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የእርሻ ስራ የጀመረው ዛሬ በሰፈረበት አካባቢ ከረጋ በኋላ ከ17ኛውና ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው። ይህ ማለት የተሰማራበት የስራ መስክ ከብት ማርባት፤ እምነቱ ደግሞ ዋቄ ፈና ነው የተባለው ኦሮሞ የማያበቅለው እህል የሚሽትበትን ወቅት ጠብቆ ሃይማኖቱ አይደለም የተባለውን መስቀልን አሳልፎ መስቀል በሆነ በሳምንቱ እህል እንዲያበቅል፤ እሸት እንዲቀምስ ለሚያስችል ፈጣሪ ምስጋና ሊያቀርብ ይችላል ካልተባለ በስቀር ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ እሬቻን ማክበር የጀመረው ሸዋን ሲወር ያገኛቸው አራሽና እህል አብቃይ የአማራ ገበሬዎች ያመረቱት ሰብል ለፍሬ እንዲበቃና እሬቻ [እሼት] እንዲቀምሱ ላስቻላቸው ፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረውን የምስጋና ባሕል በመውረስ ነው። ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም።

ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ እሬቻ የሚከበርበት የሸዋ ምድር ኦሮሞ አካባቢውን ከውረሩ በፊት በግብርና ሥራ እየተዳደረ ይኖርበት የነበረው አማራ ነበር። ይህን ታሪክ የሚነግረን ኦነጋውያን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት የኦሮሞ ታሪክ ጸሐፊ ጀርመናዊው አይኬ ሐበርላንድ ነው። አይኬ ሐበርላንድ እ.ኤ.አ. በ1963 ዓ.ም. “Galla Süd-Äthiopiens ” በሚል በጀርመንኛ ባሳተመው መጽሐፉ ገጽ 786 ላይ እንዲህ ይላል፤
 
"Im Herzen Äthiopiens, in Regionen, die einst von den Amhara besetzt waren, lebt die Shoah Galla, die oft als Tullema bezeichnet wird."
 
የእንግሊዝኛ ትርጉም፤
 
“In the heart of Ethiopia, in regions once occupied by the Amhara, live the Shoa Galla, often referred to as the Tullema” [2]
 
የአማርኛ ትርጉም፤
 
“በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የአማራ ይዞታዎች በነበሩ አውራጃዎች ውስጥ ቱለማ የሚባሉ የሸዋ ኦሮሞዎች ይኖራሉ”
 
እንግዲህ! የኦሮሞ ብሔርተኞች በሙሉ በፈጠሩት ተረት እየተመሩ “ እሬቻን ከ150 ዓመታት በፊት ይከበር ወደነበረበት ወደ ፊንፊኔ መልሰነዋል” የሚሉን በታሪክ የነሱ ወዳልነበረው ቦታና ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ባላርሥት የነበረው አማራ ያከብረው የነበረውን የሰብል ክብረ በዓል ወርሰው ነው። እሬቻ በእውነት የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ [ከወያኔና ኦነግ ዘመን በፊት] ክብረ በዓሉን ከሁሉ በፊት መከበር የነበረበት የኦሮሞ አባት የሆነውና ዛሬም ድረስ ከብት በማርባት የሚተዳደረው ቦረን በሚኖርበት ቦረና ውስጥ እንጂ ኦሮሞ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ያገኛቸው የኢትዮጵያ ነገዶች የሚተዳደሩበት የእርሻ ስራ በሚዘወተርበት አካባቢ መሆን አልነበረበትም። በዓሉንም ማክበር የነበረበት የዘላን ኑሮውን በመተው በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የእርሻ ስራ ተምሮ የኢኮኖሚ ባሕል በመቀየር በተማረው የእርሻ ስራ ኑሮውን በመሰረተው ልጁ ቱለማ ሳይሆን የኢኮኖሚ ባሕሉን ሳይቀይር ዛሬም ድረስ ኑሮውን ከብት በማርባት የሚገፋው አባቱ ቦረን መሆን ነበረበት።

 በዚህ ላይ ከቱለማም ኦሮምኛ ተናጋሪ ሁሉ ኦሮሞ አይደለም። ከቦረና ውጭ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። የተቀረው ኦሮምኛ እንዲናገር የተደረገው ተገዶ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Salgan Borana, sagaltamman gabra» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርባ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው። ባጭሩ እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ከሁሉ በፊት መከበር የነበረበት “Salgan Borana” የተባሉት በሚኖሩበት አካባቢ እንጂ “sagaltamman gabra” በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ መሆን አልነበረበትም። እንዴውም እሬቻ ከዘመነ ወያኔና ኦነግ በፊት “Salgan Borana” በተባሉት እውነተኞቹ ኦሮሞዎች ዘንድ አይታወቅም።
 
ባጭሩ እሬቻ ኦሮሞ በወረራ ከያዘው ከገርባ የተዋሰው እንጂ አባቱ ከሆነው ከቦረና የወረሰው አይደለም። ከመስቀል በኋላ በእርሻ የሚተዳደር ማኅበረሰብ ያከብረው ከነበረው የምስጋና ቀን ከሆነው ከእሬቻን ሥነ ሥርዓት ውስጥ የኦሮሞ የሆነው የኦሮሞ የገዢ መደብ እሬቻን ከሌሎች ወርሶ የራሱ ሲያደርግ ከቃልቻና ባዕድ አምልኮ ጋር የቀላቀለው ነገር ብቻ ነው። ለዚህም ነው ዛሬ እሬቻ ሲከበር ዛፍ ወትተና ቅቤ እየተቀባ፤ መስዕዋት እየቀረበ [በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን እሬቻን ሲያከብሩ ሰው በማረድ መስዕዋት ያቀርቡ እንደነበር በዘመኑ የተመዘገበ የታሪክ ማስረጃ አግኝቻለሁ] ዋቃ ከሚሉት ቃልቻ ጋር ቀላቅለው እያከበሩት የሚገኙት። ይህም በመሆኑ ነው ኦሮሞ እሬቻን ሲወርስ ወደ ባእድ አምልኮና ሃይማኖት በመቀየሩ የተነሳ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ሳይቀር እሬቻን ሃይማኖታዊ ሥርዓት አድርጎ ሊያቀርበው የቻለው።
_____
የግርሜ ማስታወሻ፤
 
[1] ትርጉም፡ ግርማ በሻህ in [አምሃ ዳኘው (2012)፥ ሐገራዊ ብሔርተኝነት እና ዘውጋዊ ብሔርተኛነት በኢትዮጵያ፥ ገጽ 118]
[2] ዝኒ ከማሁ፥ ገጽ 171.

Read more