ወልቃይት ለም ነው፡፡ ብዙዎች እንደሚስማሙበት በመላው አማራ ምድር ዋናው ምርታማ አካባቢ ወልቃይት ጠገዴ እና አካባቢው ነው፡፡ የትግራይ ሪፐብሊክ ሲታሰብ ከላኮመልዛ እና ጎንደር የሚወሰዱ መሬቶችን ተማምኖ ነው፡፡ ከእነዚህ ሁለት አካባቢዎች ውጭ ትግራይ ማለት ድንጋይና ብናኝ ናት፤ ናሳ የሚለቀውን የማርስ ፎቶ የምትመስል፡፡ እኔ ራሴ እስከማውቀው ትግራይን በደን ለመሸፈን ያልተደረገ ጥረት አልነበረም፡፡ የሚተከለው ችግኝ ግን አንዱም አይጸድቅም፡፡ በመጨረሻ ተራራዎችን ከልሎ ማስቀመጥ እና የሚለሙ ከሆነ ዝም ብሎ ማየት የሚል ስልት ቀየሱ፡፡ እስካሁን ተራሮችን ከልለው ምናልባት የሰሀራ በረሀ ነፋስ ዛፍ አምጥቶ ዘርቶ ያበቅልልን ይሆናል ብለው እየጠበቁ ይሆናል… ቅቅቅ ለምለሚቷ ኣደይ ትግራይ፡፡ የድንጋይ ሪፑብሊክ መመስረት ስለማይቻል እንግዲህ ወያኔዎች አለቅጥ ሊያስፋፏት ግድ ነበረባቸው፤ አለባቸው፡፡ እንደሚመስለኝ የመጀመሪያው ዙር ከዚህ በፊት የተወሰዱትን የአማራ መሬቶች ይዞ የትግራይን ሀይል መገንባት እና ሌላ አቅም ሲገኝ በሶስተኛ ዙር ከፊል ጎንደርን፤ እስከ አምባጊዮርጊስ ድረስ፤ በላኮመልዛ በኩል ደግሞ ወልድያ ድረስ መውሰድ የሚል እቅድ ነው፡፡ ሶስተኛው ዙር እስከ ታላቁ አባይ መድረስ ነው፡፡ ያው ግድብ እየገነቡ አይደል ሱዳን ጥግ፡፡ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው ግን በሰላም እንዳልሆነ ያውቁታል፡፡ ለዚህም ብዙ እርምጃ መጓዝ ነበረበቻው፡፡ ሁሉም እርምጃቸው ጸረ አማራ ነው፡፡
እርምጃ አንድ
ኢትዮጵያን መቆጣጠርና የትግሬ ከበርቴ መደብ መፍጠር፡፡ የገንዘብ አቅማቸውን በመገንባት የፖለቲካ ስልጣናቸውን በዚሁ ገንዘብ በመታገዝ ማራዘም፡፡ የፖለቲካ ስልጣናቸው መራዘሙ በሚያመጣላቸው እድል የገንዘብ አቅማቸውን የበለጠ ማዳበር፡፡ በዚህም መሀል በተቻለው መጠን ሁሉ እያንዳንዱን ትግሬ ማብቃት፡፡ ማብቃት ማለትም በኢኮኖሚና በማናቸውም በሌላው ረገድ ነው፡፡
እርምጃ ሁለት
የመላውን ኢትዮጵያ ገንዘብ በመቆጣጠር የትግሬ ከበርቴ መፍጠሩ ትግራይን ከማልማት ጋር በቀጥታ ይያያዛል፡፡ በዚህም ትግራይን የማበልጸግ ሂደት ጠቃሚው አስተሳሰብ የወራሪነት መንፈስ ነው፡፡ ወራሪ ወይም ቅኝ ገዥ ጥሬ እቃ ወደራሱ አገር በማጋዝ ወደፋብሪካ ምርትነት ለውጦ መልሶ በውድ መሸጥ ነው፡፡ በዚህም ስሌት ትግራይ ውስጥ ፋብሪካዎችን በማስፋፋት ለትግሬ የስራ እድል መስጠት እና ከሌላው ኢትዮጵያ ጥሬ ሀብትን በነጻም ሆነ በርካሽ በማጋዝ ፈብርኮ መልሶ በውድ መሸጥ ነው፡፡ እየተደረገ ያለውም ይሄው ነው፡፡
እርምጃ ሶስት
አማራውን ማደህየት፡፡ በንግድም፤ በትምህርትም፤ በሌላ ዘርፍ የአማራን ህዝብ ማፈን እና በተለያዩ ዘዴዎች ማደህየት፡፡ አማራን ማደህየት ለትግሬ መንግስት ፊታውራሪዎች ምን ምን በጎ እድል እንደሚፈጠርላቸው እና እንደፈጠረላቸው መመርመር ነው እንግዲህ፡፡
እርምጃ አራት
አማራውን ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት በታሪክ ጥፋተኛ እንደነበረ እና ጥፋተኝነት እንዲሰማው እና አማራነቱን እንዲሸሸው ማድረግ፡፡ ይህም የሚደረግበትን የዘር ማጥፋ ወንጀል አማራ ነኝ ብሎ በጋራ እንዳይከላከል ያደርገዋል፤ አድርጎታልም፡፡ በረቀቀ ዘዴ ትግሬ እና ሌሎች ብሄሮች ከየራሳቸው ብሄር ጋር ፍቅር ውስጥ ሲወድቁ አማራው ግን አማራነቱን እንዲሸሽ እና ተበታትኖ እዲቀር ሆኗል፡፡ አማራው እንደአማራ ቢመክት ያሰቡትን መስራት እንደማይችሉ የተረዱት ወያኔዎች ይህንን የአማራነት ስሜት ማጥፋት እና በአማራነት መሰብሰብ እና ስለአማራነት መናገር እንደጥፋትና ነውር ነገር እንዲቆጠር ማድረግ ዋና ስራቸው ሆነ፡፡ የዚህ ስውር አላማቸው ደጋፊም አላጡም፡፡ በተለምዶ ራሳቸውን የአንድነት ሀይል ብለው የሚቆጥሩ፤ ከፊሎች በስህተት፤ ሌሎች ደግሞ በመሰሪነት ይህንን የወያኔ ጸረ አማራ ስሜት ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡ ከእነዚሁም አንዱ አማራ በብህሩ ከተደራጀ ኢትዮጵያ አለቀላት የሚለው ጎደሎ አስተሳሰብ ነው፡፡ እነዚህ መናኛ ፖለቲከኞች እና ስሁታን ምሁራን የአማራ አንድ ላይ መሆን በምን ሂሳብ ኢትዮጵያን ከማፍረስ ጋር እንደተገናኘ ሊያስረዱ አይችሉም፡፡ “አማራ መደራጀት የለበትም፤ ከተደራጀ አገር ይበትናል” የሚለው ስንኩል አስተሳሰብ አማራ ላይ ያደረሰው ተጽእኖ ወያኔ በግልጽ ከሚያካሂደው ጸረ አማራ ቅስቀሳ ጋር ቢተካከል እንጅ አያንስም፡፡ የእነዚህን መናኛ ፖለቲከኞች እና ስሁታን ምሁራን ጸረ አማራ ቅስቀሳም ወያኔ በራሱ መንገድ አማራውን ለመበታተን እና እንዳይሰባሰብ ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡ “አማራ መጣባችሁ እንደድሮው ሊጨቁናችሁ ነው፤ የድሮውን ስርአት ሊመልስ ነው” እያለ እየዞረ የሚቀሰቅሰው ቅስቀሳ የዚሁ ጎደሎ ሀሳብ ተቀጥላ ወይም ደሚራ ውጤት ነው፡፡ መናኛ ፖለቲከኞች እና ስሁታን ምሁራን የሚያስተጋቡት ይህ “አማራ ከተደራጀ አገር ያፈርሳል” የሚል ቅስቀሳ ለወያኔ ጉልበት ፈጥሮለታል፤ አማራ ላይ ለሚያደርገው የሀሰት ክስም ምክንያት ሆኖለታል፡፡ በታሪክ የምናውቀው ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡ አማራ ተሰባስቦ ሀይል ባገኘባቸው ጊዜያት ሁሉ አይደለም ኢትዮጵያዊ አለም አቀፋዊ አንጸባራቂ ድሎችን ነው ያስመዘገበው፡፡ ይሁንና በዚህ ጎደሎ አስተሳሰብ የተነሳ አማራ በዛ በኩል በወያኔ፤ በዚህ በኩል በአንድነት አቀንቃኝ ተብየዎች እግር ተወርች ታስሮ ቆየ፡፡ አእምሮ ያለው ሁሉ አማራው በአማራነቱ አለመሰባሰቡ የወያኔን እድሜ እዳራዘመው እና ያልጠበቀውን ጉልበት እንዳጎናጸፈው ይረዳል፡፡
እርምጃ አምስት፡- አማራን መሸበብ
አማራን መሸበብ አማራን የማጥፋት እና የትግሬን መንግስት እውን የማድረግ ሂደት ዋናው ዘዴ ነው፡፡ የአማራ መሸበቢያ ሆነው ያገለገሉትም ወልቃይት ጠገዴ እና የድሮው ራስ ገዝ ወሎ ምስራቃዊ እና ሰሜናዊ ክፍሎች ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው ትግራይ አለማቀፍ ድንበር የላትም፡፡ ምናልባት አሁን በትግሬና ኤርትራ መካከል ያለው ያልተከለለ ድንበር ካልተቆጠረ በቀር፡፡ ትግራይ በምስራቅ በኩል ከቀይ ባህር ወደ ውስጥ ገባ ብላ በመገኘቷ የባህር በር ችግር አለባት፡፡ ይህንንም ለመፍታት አሰብን በሻእብያ እጅ በይደር በአደራ መልክ አስቀምጠውት እንደነበር ይጠረጠራል፡፡ ምክንያቱም ሸዋን ወይም መሀል አገርን ከቀይ ባህር መነጠል እና መልሶ እዳያንሰራራ ማድረግ የሚለው ቀዳሚ የወያኔ አጀንዳ ስለነበር ከአሰብ ሆነ ብለው ነጥለውታል፡፡ ስለሆነም ከወሎ ቆርሶ አፋር ብሎ ሌላ ክልል መፍጠርና ያንን ክልል በሂደት የትግራይ ክፍል አድርጎ የባህር በር ማግኘት አንዱ ድብቅ አጀንዳ ነው፡፡ ምናልባት ከኤርትራ ጋር አሁን ስለተጣሉ የአሰብን ጉዳይ አስቸጋሪ ያደርገዋል የሚሉ ይኖራሉ፡፡ ነገሩ ትክክል ሊመስል ይችላል፡፡ ይሁንና አንዱ ወዳጃችን እዳለው “የሻዕብያን እና የወያኔን ሴራ እንኳን ሰው ሰይጣን አይደርስበትም”፡፡ ዞሮ ዞሮ ትግራይን ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ሀያል መንግስት ማድረግ ማለት ከኤርትራ ጋር የሚኖራቸውን የጥቅም ድርድር አቅም ያሰፋዋል ማለት ነው፡፡ በዚህም ስሌት በቀላሉ የባህር በር ማግኘት ይችላሉ፡፡ ወይም ታላቋን ትግራይ ከፈጠሩ በኋላ ከኤርትራ ጋር በመቀላቀል የጥንቱን የትግራይ ትግርኝ ሪፐብሊክ ህልም ያሳኩ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል? አለም እንደሆነ ተለዋዋጭ ናት!
ወደሁለተኛው እና ዋናው የአማራ መሸበቢያ ወልቃይት ስንመጣ ለትግራይ መንግስት ወልቃይት ጠገዴን፤ ሁመራን፤ ዳንሻን፤ እና ወዘተ መቆጣጠር ብዙ እድል ይፈጥርለታል፤ ፈጥሮለታል፡፡ ከሱዳን ጋር በመገናኘት አለም አቀፍ ድንበር ማግኘት አስችሎታል፡፡ ይህ አሁን በግድ ወደትግራይ የተቀላቀለው ምድር አማራ በጎንደር በኩል ሱዳንን ወደምእራብ በመታከክ ከኤርትራ ጋር የሚገናኝበት ነው፡፡ ይህንን በመቁረጥም ምናልባትም አማራ ከኤርትራ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ማቋረጥ ያስችላቸዋል፡፡ ወልቃይትን መቆጣጠር በሌላ ጎኑ የአማራን ዘር የማጥፋቱ አንዱ አካል ነው፤ የቻለውን ያህልም አጥፍቷል፡፡ በተጨማሪም መሬቱ ለም በመሆኑ የኢኮኖከሚ ጡንቻውን ያዳብርለታል፤ አዳብሮለታል፡፡ በተዘዋዋሪም የአማራን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያዳክማል፤ አዳክሟል፡፡ አማራ በወልቃይት በኩል ከኤርትራም ሆነ ከሱዳን ጋር የሚኖረውን ግንኙነት በማቋረጥ፤ ቀስ በቀስም መተማን እስከ ቤኒሻንጉል ድረስ በመውሰድ የአግዳሚ ወንበር ቅርጽ ያላትን ትግራይ መፍጠር አማራን አኮስምኖ፤ አዳክሞ ያስቀረዋል፡፡ በመጨረሻ ለሚደረገው የዘር ማጥፋት ሂደትም ያመቻቸዋል፡፡ ምክንያቱም አማራው መሀል ላይ ታፍኖ በየትም መላወሻ እንዳያገኝ ስለሚደረግ አቅም አልባ ሆኖ ከመጥፋት በቀር ሌላው እድሉ የመነመነ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ሽበባ በተጨማሪ ከማንኛውም ብሄር ጋር እንዳይተባበር እና መውጫ ቀዳዳ እንዳያገኝ ከሌሎች ብሔሮች ጋር ቁርሾ ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ አማራ ላይ ለሚደረገው የመጨረሻ ጥፋት ይረዳ ዘንድም በየቦታው እየዞሩ የጥላቻ፤ የበቀልና ቂም ሀውልት ይተክላሉ፡፡ እንግዲህ ማንኛውም አማራዊ ሀይል ወያኔን ለመፋለም ከመነሳቱ በፊት ይህንን ሽበባ ወይም ከበባ እንዴት መስበር እንደሚችል በጥልቀት ማሰብ አለበት፡፡ ቤተ አማራ የዚህን መፍትሄ ይዞአል፤ ተግባራዊ ለማድረግም የመላውን አማራ ንቁ ተሳትፎ እና እገዛ ይጠይቃል፡፡
እናም አማራ ሁሉ ወልቃይት ላይ የሚደረገው የአንተን ጉርቦ ለማነቅ እንጅ ወልቃይትን ብቻ ወስዶ የማይቀር መሆኑን አውቀህ ለራስህ ስትል ከራስህ ጎን ከወልቃይት አማራ ጎን ተሰለፍ፡፡
አገራችን አማራ ወንዛችን ተከዜ፤
ማን ያስገድደናል እምቢ ያልን ጊዜ፡፡
ትክክል ነህ ቤተአማራ በርቱ ፍጠኑ፣ በውጭ አገር የሚገኙ አማራዎችን አስተምሩ፣ከቤተአማራ ጎን አሰልፉ፣አገር ውስጥም በስፋት ተንቀሳቀሱ።ወታደራዊይ ትግልም ያስፈልጋል።
ReplyDelete