Open top menu
June 29, 2017
ይድረስ፦ መስመራችሁን ስታችሁ እዋዠቃችሁ ለምትገኙ አማሮች

(Gizenew Demelash)

1. ግንቦት ሰቦት በሚባል ፀረ አማራ ድርጅት ውስጥ የተሰገሰጋችሁ ጥቅመኛ የአማራ ተወላጆች

2. "የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል የኦነግን፣ ህውሃት እና መሰሎቻቸው አማራን የመክሰሻ ድርጅት መሰረትን ለምትሉን አማሮች

3. በሀገረ ቤት ሆናችሁ በምርጫ ቦርድ አበል በመሿሿም እና መሻሻር ላይ ብቻ ለተወሰናችሁ እና አማራነትን እንደ መውረድ ቆጥራችሁ ለምትመፃደቁ የትግል እንቅፋቶች

4. ዛሬም የዋለልኝን ፈለግ በመከተል ከፀረ አማራ ድርጅቶች አጀንዳ በመቀበል አማራን በጎጤ ማህበራት ለመከፋፈል እየሰራችሁ ለምትገኙ ጭንጋፎች

5. ኢሳት በተባለው የፀረ አማራ ሀይሎች ሚዲያ ውስጥ ተሰግስጋችሁ እንደ ይሁዳ አማራነትን ስታሻሽጡ ለምትውሉ የአማራ ተወላጆች

6. ለዚህ ትውልድ በይፋ የተገለጣችሁ የዘመናችን ዋለልኞች፦ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አቻምየለህ ታምሩ፣ አቶ ደመቀ ገሰሰ የኔዓየሁ፣ አቶ ሙሉነህ ዮሀንስ (አስናቀው አበበ/ህዝብ ያሸንፋል) ... ለአብነት

“ኦሮሚያን” አገር የማድረጉ ሂደት አዲስ አበባን ለኦሮሞች በማስረከብ ዛሬ ተጠናቋል። “አዲስ አበባ ኬኔ” ብሎ የተሰለፈና ፀንቶ የታገለው የኦሮሞ ብሔርተኛ እንደ ሁሌው ዛሬም ከጠየቀው በላይ አፈሰ። የአማራ ኢሊት ነን የሚሉ የተማሩ ደንቆሮዎች “የኢትዮጵያ እንጂ የአማራ ብሔርተኝነት የሚባል ነገር የለም” እያሉ አፋቸውን ሲያሰፉ ከወሬ ይልቅ የፖለቲካ ስራ ላይ የተጉት ትውልዳቸውን በብሔርተኝነት የቀረፁና ያደራጁ የኦሮሞ ኢሊቶች በድል ላይ ድል እያስመዘገቡ ከባዶ ተነስተው የአገር ባለቤት ለመሆን በቁ። እኛ ደግሞ የኛ የሆነውን ሁሉ እያጣን አለን።


የዛሬ 25 ዓመት እነ ወልቃይትን፣ እነ ጠገዴንና ጠለምትን፣ እነ ራያና ቆቦንን፣ እነ መተከልን ፣ ከፊል ሸዋን ለሌሎች አሳልፎ የሰጠ የአማራ ሕዝብ ጠላት የሆነው ብአዴን ዛሬ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ባልመከረበት ሁናቴ አዲስ አበባን ለኦሮሞቹ ፈርሞ በማስረከብ የአባቶቻችንን ዕርስት አስነጠቀን። ብአዴን የህውሃት ክንፍ መሆኑን አጥቸው አይደለም። በስማችን እየነገደ ያለ ቡድን ከመሆኑም በተጨማሪ ቢያንስ በማከዕከላኛውና ከታች ባለው አባላት ዘንዳ አማራዎች አሉ በሚል ነው። መችም አሳዛኝም አሳፋሪም ታሪካዊ ክስተት ነው። እውነቱን ለመናገር ወደ 50+ ዓመታት ለሚጠጉ ግዜዎች የሚቆረቆርለት እና ዛሬን ሊመክት የሚችል ድርጅት ማቋቋም የተሳነው ኢሊት ያፈራ ሕዝብ በአለም ላይ ከአማራ ውጪ ሌላ ሕዝብ የሚኖር አይመስለኝም።

ይሄ ሀቅ እኔን ሁሌም የሚያሸማቅቀኝ ጉዳይ ሆኖ አለ። አማራ እንደ ሕዝብ ዛሬ ባለበት ሁናቴም ቢሆን ህልውናው ያለሁ በወለዳቸው ጭንጋፍ ልጆቹ ሳይሆን በአዛውንቶች ፆምና ፀሎት ብቻ ነው። ይሄ እውነታም አጥንቴ ድረስ ዘልቆ የሚሰማን እውነታ ነው።"መሬት ሲያረጅ ሙጃ ያበቅላል" ይባላል። በራሳቸው፣ በዘራቸውና በብሔራቸው የሚሸማቀቁ፣ ጣታቸውን ወደታላላቆቹ ከመቀሰር ባለፈ "የኔ" የሚሉትና የሚሞትቱለት ግብ የሌላቸው፣ በቆልማማ ብዕራቸው አይናቸውን ጨፍነው ዙሪያቸውን ከመጨርገድ ባለፈ ይሄ ነው የሚባል ትልም ለመተለም የማይችሉ ፣ የነሱ መደንዘዝ ሳያንስ የወንድሞችን እቅድ ለማክሸፍ ሌት ተቀን የሚተጉ ፣ እንደ ሰው ራዕይ የሌላቸው "ሙጃ" ግለሰቦች በዙብንና የሕዝባችንን ጣር አረዘሙት።

ለማንኛውም መጪው ግዜ ከዛሬው እጅግ የከፋ ነውና አማራ ከታረደባቸው እንደ ጅማ ካሉ አካባቢዎች ሸሽተህ አዲስ አበባና ዙሪያዋ የከተምክ አማራ ወገብህን አጥብቀህ እሰር። ሞርተኛ ለመሆን አይደለም። ፈርቿ እያስፈራራሁም እንዳይመስላችሁ። አማራን በብሔርተኝነት የማሰባሰቡ ትግል አማራ ነን ብለው ሰይፍ የመዘዙበትን ውራጅ አማራዎች ለመሻገርና የአማራን ሕዝብ ከጥፋት ለመታደግ ከገመትነው በላይ ግዜ እንደሚዎስድብን ስለተገነዘብኩ ነው። የነቃው እና የአማራን ሕዝብ በብሔሩ እያሰባሰበና እያደራጀ ያለው የአማራ ኢሊት በስንት ድካም ያሰባሰበውን ሕዝብ ለመበተን ሌት ተቀን እየጫጫረ ያለውን ሌላኛውን አማራን ለማሸነፍ የሚደረገውን ትግል እጅግ አድካሚና አሰልቺ መሆኑን ቀርቤ አይቻለሁ።

ለማንኛውም #ቤተአማራ ለአማራ ብቸኛ መድህን ናትና ጠበቅ እናድርጋት።
Read more
June 28, 2017
አዲስ አበባ ፤ የሸዋ አማራዋ መዲና - “”የአባቶችን ርስት አልሰጥም!!!!!”

አዲስ አበባ፤ ሸዋ የአማራዋ መዲና ናት ስንል....

ኢህአዴግ በአሁኑ ውሳኔው የኦሮምያን ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ ለማስከበር አረቀቅኩት ያለው አዋጅ ፤ በእርግጥም እንደሚፀድቅ ተማምኖ ማቅረቡ ፤ ያልበሰለ እና ታሪካዊ የአማራን ድርሻ እና ባለቤትነት ያገለለ አሰተሳሰብ በመሆኑ ሊታረም ፣ ሊታይ እና ሌሎችም በሄሮች እና ብሄረሰቦች እንዲሁም ፣ የሽዋ አማራው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ወንበር የመወሰን መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። አዲስ አበባ አማራው ራሱን ሰውቶ ያነገሳት ከተማ ናት። ለአማራው ልዩ ጥቅምም በአዲስ አበባ ከምክር ቤት ወንበር ጀምሮ እስከ ሰሜን ሽዋ የአማራ ክልል ዞን ልዩ ተጠቃሚነት የታሪክ ባለቤትነቱ ሊገለል አይገባም።


"የአማራ" መንግስት ስርዓት ውስጥ "የሸዋ አማሮች" አዲስ አበባን መርጠው ፣ ቆርቁረው ፣ አደራጅተው እና አሳድገው ለሀገር እና ለአለም ዲፕሎማሲያዊ መቀመጫነት አብቀተዋታል የ"ብሄረተኞነት"ከተማ ሳይሆን የሁሉም ብሄርች ከተማ መናገሻ አድርገዋትል። ይህ አፈታሪክ አይደለም ማንበብ ለሚችል ሰው Sorenson, Imagining Ethiopia , (New Brunswick, NJ Rutgers University Press) p.12 ወይም Messay, p.36 ፣ እና Ibid., p.23 እንዲሁም Taddesse,1972,pp 132 -135; Bahiru, p.75; Donald, C.pp.21 -22 ያገላበጠ አንባቢ ሁሉ አያጣውም። ብዙሃኑ "የሸዋ አማራ" ያቆማት እና ዙፋኑን ያፀናባትን ከተማ የአንድ ብሄር ተጠቃሚነትን ብቻ ባረጋገጠ ሁኔታ ከፖለቲካዊ ቁማርነት እየገፉ ፣ የአንድ በሄር እንብርት ናት። ሲሉ ማውራት ለኔ ትንሹ ልጅ ሲያለቅስ ትልቁን አንተ ዝም በል ብሎ የትልቁን ንብረት ቀምቶ እንደመስጠት ነው ምቆጥረው ። 



አዋጁ ፍትሃዊ ማይሆነው እኩል ተጠቃሚነትን ሳይሆን የአንድ ቡድን ውቅታዊ ጥያቄ ለመመለስ ያለመ መሆኑ ላይ ማተኮሩ ነው። በእርግጥም የመንን ፣ ቀይ ባህርን ፣ ኤርትራን እና ጅቡቲን አንድም በአቅም እጥረት አልያም በፖለቲካ ድክመት እያሳለፍን ታሪካችንን ሽጠን በልተነዋል። ከታሪካዊ ባለቤትነት ይልቅ የፖለቲካ ጥቅም የሚያሸንፈው መንግስት በተፈጠረበት ጊዜ ሁሉ ብዙ ነገር ከእጃችን ወድቋል። ሀገርን መገንባት ሳይሆን ብሄርን በመገንባት በተጠመደ ስርዓት ውስጥ ደግሞ አንድን በር መዝጋት ብዙ ሽህ በሮችን እንደመክፈት ይቆጠራል ይታያልም። አዲስ አበባን መስርተው ፣ ጠቅመው ፣ የመንግስት አመራር መዋቅር ሹመው፣ አብዛኛውን የኢኮኖሚ ምንጮች አፍልቀው፣ የአዲስ አበባን የግዛት ክፍሎች ይገዙ የነበሩ፣ የአዲስ አበባ መስራች ና ፈጣሪዎች ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸው አዲስ አበባን ማዕከል አድርገው የመሰረቱ ነበሩ። የአማራ ህዝብ የሸዋ መኳንንቶች ምስጋና ይግባቸው እና የሁሉም ብሄሮች መኖሪያ አድርገዋታል።


በቅርቡ በተካሄደ ጥናትም የብሄር ማንነት የሌለው ሰፊ ህዝብ የሚኖርበት ክልል አዲስ አበባ ነው። ከ63 በመቶ በላይ የሚሆነው አማራ በሆነባት ከተማ መሬቱን የአንድ ብሄር ሃብት አድርጎ ማውጅ ምን አይነት ብስለት የጎደለው አሰራር መሆኑን ያሳያል።


ብዙሃኑ የሸዋ አማራ በድህነት እየኖረ ስልጣን አልባና እንደ አንድ ቡድን በየስርዓቱ እየተመዘበረ ባድማው ውስጥ ራሱን መፈለግ ወጋችን ፣ ታሪካችንም ነው። ይህ አዲስ አበባ ባለዎለታዋን የምትዘነጋ ከተማ አይደለችም ለእምየ ሚኒልክ ሃውልቷን ፊቱን ኦዞራ ያቆመችው በምሃል ጊዩርጊስ ወደ መንበሯ "የሸዋ አማራ ሀገር" ነው። ታዲያ እንዴት ነው በኦሮሞ የተከበበችው አዲስ አበባ ፊንፊኔ ብቻ ምትሆነው። ቋንቋዋን ምትቀይረው። የሌላው ብሄር ልጆችስ በአባታቸው ባድማ ወዴት ይወድቃሉ???


የማይመለሱ ብዙ ሽህ ጥያቄዎች ቢኖሩም ያባቶቻችንን ርስት አንሰጥም ብያለሁ እና አማራ አዲስ አበባን የሚያውቃት ማንም ከሚያውቃት በፊት ነው። Pankhurst Rassam አገላለጽ ጎንደር በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አጋማሽ ከሰሜን፣ ከምእራብና ከደቡብ ለሚነሱ የሲራራ ነጋዴዎች ሁነኛ ማረፊያ ማዕከል ነነበረች በዚያ ዘመን ከጎንደር ወደ ማህል አገር የሲራራ ነጋዴዎች መተላለፊያ በርካታ አቅጣጫዎችና ቅርንጫፎች ነበሩት። በዚህም አንዷ አዲስ አበባ እንደነበረች በመፅሓፋቸው ከትበውታል።


ከጎንደር ሰፈራቸው የተነሱ ነጋዴዎች በጣና ሃይቅ በኩል አድርገው ወደ ይፋግ ከተሻገሩ በሁዋላ በሁለት በመከፈል አንዱ ወገን ወደምስራቅ አቅጣጫ ወደ ሸዋ (አዲስ አበባ) ሲያቀና ሌላኛው ወገን ደግሞ ወደደቡብ ወደ ጎጃም ያመራል። ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚዘልቀው የንግድ መስመር፣ ባሶ፣ ጉድሩ፣ በማቋረጥ ወደ ጎንደር መጥተው በጨውና ከውጭ አገር በሚገቡ እቃዎች የሚለወጡ "ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ የከርከሮ ቀንድ፣ የግስላ/ ነብር ቆዳ፣ የጉማሬ ቆዳና ጋሻ እንዲሁም የባሮች" ምንጭ ወደሆኑት ከፋና ጃንጀሮ ይደርሳል ። ከእነዚህ በተጨማሪ ነጋዴዎች በሸዋ (አዲስ አበባ)፣ በሐረርና በዘይላ በኩል በማለፍ ወደ ሶማሌ የበርበራ ወደብ፣ "የዝሆን ጥርስ፣ ባሮችና ፈረሶች" ይዘው በመሄድ በልዋጩ ብረት፣ ጥጥና የህንድ ሸቀጦችን ለአገር ውስጥ ገበያ ያቀርቡ ነበር ።


አገር አቋራጭ ንግድ ወይም የሲራራ ንግድ በአማራ ክልል ለነበሩት በርካታ ገበያዎችና የንግድ ማእከላት መፈጠር ዋንኛ ሚና ተጫውቷል። በ18ኛውና በ19ኛው ምእተ አመታት የጎንደር ፣ የጎጃም እና የሽዋ ነጋዴዎች ምቹ መደላድል የፈጠሩባት እና ጠምደው ያረሱበት ርስታቸው ናት።


ለመሬት ባለቤትነት ታሪክ ተያይዞ የሚጠራው የንግድ መስመር ሲሆን በ19ነኛው ምእተአመት መጀመሪያ ላይ ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከነበራቸው የንግድ መስመሮች የሸዋው የንግድ መስመር ነው። አጼ ሚኒልክ የመንግስታቸውን መቀመጫ ከተማ ከአንኮበር ወደ እንጦጦ ከማዘዋወራቸው በፊት አንኮበር፣ አንጎለላና አልዩ አምባ የታወቁ የገበያ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል። በተለይ አንጎለላ ወደ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምእራብና ደቡብ የሚጓዙ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የጉራጌ፣ የሐረሬና የደንከሌ ነጋዴዎችን ቀልብ የሚስብ የንግድ ማእከል ነበር።
ከሸዋ የንግድ መስመር ወደሰሜን አቅጣጫ በአድዋና በአንጣሎ አድርጎ የጎንደርና የሸዋ ሲራራ ነጋዴዎች መገናኛ ወደነበረው ምጽዋ የሚደርስ ነበር።


የጎጃም ነጋዴዎችም ወደ ሰሜን የሚያልፍ ሌላ የንግድ መስመርም ነበራቸው። ከዳንግላ ባሪያ፣ ከዘጌ ቡና ጭነው ወደ ጎንደር የሚነግዱ ነጋዴዎች በቡሬ፣ በዳንግላ ወይም ዘጌ በይስማላና በደልጊ አድርገው ወደ ጎንደር ይደርሳሉ። ከወሎና ከምስራቅ ጎጃም የሚነሱ ነጋዴዎች ደግሞ በደጀንና በብቸና በኩል አድርገው እንጦጦ ይሰፍራሉ። በሞጣ፣ አዴት፣ ወረታ አድርገው የሚጓዙት ወደ አገራቸው ወደ ደሪጣ የሚገቡት ነጋዴዎች ጭነታቸውን ደሪጣ ካላራገፉ በእንፍራዝና በምንዝሮ በኩል ተሻረው ጎንደር ይገባሉ። ወደ ታጁራ ወደብ የሚነግዱ የወሎና የአማራ ሳይንት ነጋዴዎች ደግሞ በብቸና፣ ቃሉ፣ ወረሂመኑና ደሴ አድርገው ይጓዛሉ። ንጉስ ተክለ ሃይማኖት በ1878 ዓም በእንባቦ ጦርነት በአጼ ምኒሊክ ድል እስከሆኑበት ድረስ ባሶ የደራ የንግድ ማእከል በመሆን አገልግሏል። የጎጃም የሽዋ እና የጎንደር ነጋዴዎች ማረፊያ ከነበሩት የሽዋ አማራ መስመርም አዲስ አበባ ቀደሚ ናት።


የንግድ መስመሮችና ማዕከሎች እድገት በ20ኛው ምዕተ ዓመት እና የአዲስ አበባን ታሪካዊ የአማራ ባለቤትነት ከምንጩ እንመርምረው።


የሽዋ አማራ መናገሻዋ አዲስ አበባ በአማራዎች መቆርቆር የንጉሰ ነገስቱ መኖሪያ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ማዕከላዊ የንግድ ማእከልና ገበያም መጀመሪያ ከነበረበት ወደ አዲስቱ ማዕከል እንዲዛወር ዋና ምክያት ሆኗል። የአዲስ አበባ ገበያም ሸቀጦች ግብይት በብዛትና በአይነት የደራበት፣ የውጭ አገር ሰዎች እንደ አገሬዎቹ ነጋዴዎች በሰፊው የሚነግዱበት ነበር። እነዚህ የውጭ አገር ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞችም የንግድ ስራቸውን በወኪሎቻቸው አማካይነት ያከናውኑ ነበር። አዲስ አበባ ማእከላዊ ገበያ መሆኗ ከደቡባዊው የአገሪቱ ክፍሎች በአማራ ክልል ታዋቂ ወደነበሩት አሮጌዎቹ ገበያዎች የሚመጣው የገበያ ሸቀጥ እንዲቀንስ አድርጓል። በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማእከል መሆኑዋን ተከትሎ የተሰራው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር ሐዲድ 75 በመቶ ያክሉ ወደአገሪቱ የሚገባና ከአገሪቱ የሚወጣ ሸቀጥ መተላለፊያ በመሆኑ ፣ የጎጃም የንግድ መስመር ከሰሜንና ሰሜን ምእራብ ወደ አዲስ አበባ መተላለፊያ መሆኑ እንዲቀር ቀጥተኛ ተጽእኖ አድርጓል። በአንድ በኩል በመተማ በኩል ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች በስተቀር ከውጭ አገር ወደ ጎጃምና ጎንደር ገበያዎች የሚገቡ ልዩ ልዩ ሸቀጦች መጠን ቀንሷል።


ዳሩ ግን ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ዝባድ እና ቡና የመሳሰሉ ሸቀጦች ተፈላጊነታቸው በማደጉ ምክንያት የሆሮ፣ አሶሳ፣ ጊዳ፣ ቤንሻንጉል፣ ወንበራና የሌሎች የደቡብ ምእራብ አካባቢዎች ነጋዴዎች ቡሬ እየተገናኙ ሸቀጦቻቸውን በአሞሌ መለዋወጣቸው አልተቋረጠም ነበር። ስለዚህም ቡሬ በአዲስ አበባ፣ መተማና ምጽዋ ገበያዎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው የቆዳ፣ ሌጦ፣ ሰም፣ ቅቤ፣ በርበሬ ምርቶች መገበያያ ዋና ማእከል ነበረች። ከ1920ዎቹ በኋላ አስመራ ከበስተደቡብ በኩል ለሚመጡ ነጋዴዎች አንዳንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸቷ፣ በእነዚህ አገልግሎቶችና በርካሽ ዋጋ በሚገዙ ጥራት ያላቸው ሸቀጦች የተማረኩ የጎጃምና የጎንደር ነጋዴዎች እስከ ኢጣሊያ ወረራ ድረስ ወደ አስመራ እየተጓዙ ይነግዱ ነበር።


በሃያኛው ክፍለ ዘመን የንግድ መስመሮች ብቻ ሳይሆኑ ወደ ውጭ በሚላኩና ወደአገር ውስጥ በሚገቡ ሸቀጦች አይነትም ላይ ለውጥ ታይቷል። በከፍተኛ መጠን ለውጭ ገበያ ተፈላጊነት የነበራቸውን የዝባድ፣ የዝሆን ጥርስና የወርቅ ምርቶች ቡና ሲተካቸው ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ሸቀጦች ሁሉ ከፍተኛ ገበያ የነበረው ደግሞ አቡጀዲ ነበር። ሸቀጦችን ወደ ውጭ ገበያ በማውጣትና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ረገድ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የሲራራ ነጋዴዎችም ቀስ በቀስ የፈረንሳይ፣ የህንድ፣ የግሪክና የአርመን ተወላጅ በሆኑ ነጋዴዎች ተተኩ።


ከ1933 ዓም በኋላ ባለው ዘመን የነበረው ንግድ በአገር ውስጥ የተመረቱ የእርሻና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን መግዛትና መሸጥን ያካትታል። እስከዚህ ዘመን ድረስ የነበረው የውጭና የአገር ውስጥ ንግድ ግን በአገር ውስጥ በተመረቱ ምርቶች ላይ ብቻ የተመሰረተ ነበር። የአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች መቆርቆር፣ የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር ሐዲድ ግንባታ በ1907 መጠናቀቅ እና በኢጣሊያ ወረራ ዘመን የመኪና መንገዶች መሰራት ለኢንዱስትሪ ማደግ ቁልፍ ሚና የተጫዎቹ ጉዳዮች መሆናቸው ይታመናል። በሌላ አገላለጽም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የኢንዱ]ስትው ዘርፍ ሚና መጫዎት የጀመረው ከነጻነት በሁዋላ ከነበረው ዘመን አንስቶ ነው። ስለዚህም በአማራ ክልል ስለኢንዱስትሪ መስፋፋት ይዞታ የምናደርገው ውይይት ኢጣሊያ ከኢትዮጵያ ከተባረረበት ዘመን ጀምሮ ይሆን ዘንድ ተገቢ ቢሆንም የንጉሰ ነገስቱና የደርግ አገዛዞች እጅግ የተማከለ የአስተዳደር ስርዓት ስለነበራቸው የኢንዱስትሪው ዘርፍ በክልሉ ንግድ ውስጥ የነበረውን ሚና የሚያሳዩ መረጃዎችን ማግኘት አልተቻለም። እነዚህ ሁለት አገዛዞች አንድ ወጥ ፖሊሲዎች መከተላቸው የንግድና የኢንዱስትሪ ስራዎች እንዳያድጉና እንዳይስፋፉ ዋንኛ ምክንያት ሆኗል።


እስከ ኢጣሊያ ወረራ ድረስ በኢትዮጵያ የነበረው የንግድ ትስስርና ልውውጥ በአማራ ህዝብ ይሁንታ የመገበያያ ገንዘብ ታትሞ በስራ ላይ በመዋሉ፣ የንግድ ፈቃድ ምስክር ወረቀት እና የዋስትና ስርዓት በመዘርጋቱ ምክንያት ወደላቀ ደረጃ ተሸጋገረ .። በኢጣሊያና በኢትዮጵያ መንግስት መንገዶች በመሰራታቸውም ነጋዴዎች ከአንዱ የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሌላው ተንቀሳቅሰው ለመግዛትና ለመሸጥ የተሻለ ሁኔታ ተፈጠረላቸው።


የውጭ ንግድን በተመለከተ ቀደም ባለው ዘመን ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው ዝባድ፣ ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ቅቤ፣ የቀንድ ከብቶችና ጥጥ የመሳሰሉት ሸቀጦች በቡና፣ ቆዳና ሌጦ፣ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ተተኩ። ቡና ለበርካታ አመታት አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች 50% እስከ 65% የሚሆነውን ሸፍኖ በመቆየቱ ምክንያት የአማራ ክልል ለአለም አቀፍ ገበያው የነበረው አስተዋጽኦ ሊያቆለቁል ችሏል። ይህም ሆኖ ግን ክልሉ ቆዳና ሌጦና እንዲሁም ጥራጥሬና የቅባት እህሎችን በማምረት ለውጭ ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል። ዳሩ ግን እነዚህ ምርቶች በአገሪቱ የውጭ ንግድ ውስጥ የተወሰነ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ የውጭ ንግድ በጠቅላላው የአማራ ክልል አርሶ አደርን የገቢ ምንጭ በማሳደግ ረገድ የተጫወተው ሚና አነስተኛ ነው። እንዲያውም የእለት ፍጆታ ከፍተኛ የሆነውን ጤፍ ፣ ማር እና ቅቤ በማቅረብ የአዲስ አበባን ውበት መልሷል።


ወደአገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ንግድ ረገድም ቀደም ሲል በርከት ያለ ድርሻ የነበረው ጨርቃጨርቅ መካከለኛና ከፍተኛ ዋጋ በሚያወጡ ሸቀጦች ተተክቷል። ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያት ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ መናርና ወደውጭ በሚላኩ ጥሬ እቃዎች ዋጋ መውደቅ ሊከሰት በሚችለው የተዛባ የንግድ ሚዛን የሚደርሰውን የኢኮኖሚ ጉዳት ለመቀነስ መንግስት በተከተለው ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦችን በአገር ምርት የመተካት ፖሊሲ አማካይነት ነው። የዚህ ፖሊሲ ውጤት፣ የጨርቃጨርቅ ውጤቶችን መጠጦችን፣ ለስላሳ መጠጦችንና ስኳርን የመሳሰሉ አላቂ የፍጆታ እቃዎችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች ከመጠን በላይ እንዲበረክቱ አድርጓል። እነዚህ ›=ንዱስትሪዎችም በአዲስ አበባ ዙሪያ፣ የባቡር ሃዲድ በሚያቋርጣቸውና ሰፋፊ ገበያ ባለባቸው አካባቢዎች ብቻ ተከማችተው የሚገኙ ነበሩ። የአማራ ክልል ገበያዎች ደግሞ በመሰረተ ልማት አለመኖርና በየገቢ መጠን ዝቅተኛነት ምክንያት የእነዚህን ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦችን ለመተካት የተቋቋሙ ኢንዱስትሪዎች ቀልብና ትኩረት የሚስብ ስላልነበረ ክልሉ በንጉሱ ዘመን በነበረው የተዛባ የኢንዱስትሪዎች ስርጭት ተጎጅ ሆኖ ኖሯል።


በተወሰኑ የምርት ዘርፎች ላይ የተሰማሩት እነዚህ ኢንዱስትሪዎችም በአብዛኛው በውጭ አገር ሰዎች ይዞታ ስር የነበሩ ናቸው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ የውጭ ካፒታል በርካታውን መጠን መሸፈኑ መንግስት ከሚከተለው ለዘብተኛ ፖሊሲ የመነጨ ነበር። የውጭ ባለ ሃብቶችን ለመሳብ የንጉሰ ነገስቱ መንግስት ብር 200,000 እና ከዚያ በላይ የመነሻ ካፒታል የሚያስመዘግቡ የውጭ አገር ባለሃብቶችን ከትርፍ ከሚገኝ ገቢ ሊከፈል ከሚገባው ቀረጥ ነጻ የሚያደርግ ፖሊሲ ነበረው። ፖሊሲው በአንጻሩ ከፍተኛውን የንግድ ገቢ ቀረጥ መጠን ከተጣራ ትርፍ ላይ 15 በመቶ እንዲሆን፣ ትራክተሮችና ኬሚካሎች ቀረጥ ሳይከፈልባቸው እንዲገቡ ሲፈቅድ በአገር ውስጥ የሚመረቱ ሸቀጦችን በሚያስገቡ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የቀረጥ ምጣኔ የሚጥል ነበር ።


አዲስ አበባ አማራው ራሱን ሰውቶ ያነገሳት ከተማ ናት። ለአማራው ልዩ ጥቅምም በአዲስ አበባ ከምክር ቤት ወንበር ጀምሮ እስከ ሰሜን ሽዋ የአማራ ክልል ዞን ልዩ ተጠቃሚነት የታሪክ ባለቤትነቱ ሊገለል አይገባም።
Read more
የአማራ ምሁራን ከወደቁበት የአንድነት አዚም እንዲላቀቁ ፓለቲካዊ ፈውስ ያስፈልጋቸዋል!

ኃያል ሰው
ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓ.ም
ከአዲሲቷ የአማራ ምድር
ፈለገ ጊዮን
ባህር ዳር


የ1960ዎቹ የአማራ ትውልድ በሰሩት ታሪካዊ ስህተት ዛሬ የአማራ ህዝብ ለሚገኝበት ዘርፈ ብዙ ችግር ዋና ምክንያት ሆኖ ይገኛል። ዘውዳዊውን ስርዓት በጭፍንና በቂ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ እንዲወገድ የአማራ ልጆች እንደ ዋለልኝ ያሉትያሉት የተጫወቱት ሚና በአማራነት ላይ የተከፈተው የመጀመሪያው ታሪካዊ ጠላትነት ነበር። የዘውዳዊው ስርዓት በአማራ ልጆች አጃቢነት መወገድ ለአማራ ጠላቶች ሰፊ በርን ከፈተላቸው። ሶማሌ በምስራቅ፣ ሻቢያና ወያኔ በሰሜን፣ ሱዳን በምዕራብ በአገራችን ላይ ፀረ አማራና ኢትዮጵያዊ ትግል አቀጣጠሉ። የዚያ ትውልድ ታሪካዊ ስህተት በተለይም የአማራ ምሁራን ማንቀላፋት ለፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ መፈጠር ጉልህ ሚና ነበረው። በቀይና ነጭ ሽብር ሰበብ አገር ወዳድ የአማራ ልጆች እየታደኑ ተረሸኑ፣ ከአገር ተሰደዱ፣ ወደ እስር ተወረወሩ። በአማራ ማንቀላፋትና አለመንቃት በኢትዮጵያ ትቅደም ካባ ስር "አማራ ይውደም" የሚል የትግል ስልት ውስጥ ለውስጥ ተቀጣጠለ። ሻቢያና ወያኔ የደርግን ቡትቶ ለብሰው በገጠርና በከተማ አማራን የማፈንና የመግደል ዘመቻ አፋፋሙ።


እነዚያ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አንድነትና ነፃነት የተሟገቱ ብርቅዬ ንጉስ በሆያ ሆዬ ጩኸት ወደ መቃብር ተሸኙ። የአፄ ኃይለ ስላሴ በግፍ ከስልጣን መውረድና የ60 ሚኒስትሮች በአደባባይ መረሸን የአማራ ውድቀት የማንቂያ ደወል ነበር። ሆኖም ግን አማራ ከመንቃት ይልቅ በየዋህነት እራሱን በማጥቃት ከፀረ አማራ ኃይሎች ጋር ተሰለፈ። ህወኃት በ1967 ዓ• ም ሲፈጠር ዋናው ዓላማ አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፈራረስ ነበር። ወያኔም በበኩሉ ከሻቢያ በተሰጠው ተልኮ መሰረት የፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ትግሉን ለ17 ዓመታት አቀጣጠለው። ያኔም በተመሳሳይ የአማራ ልጆች ከአማራ ጠላቶች ጋር በማበር አብረው ታግለውና መንገድ መርተው ወያኔን ለዙፋን አበቁት።

ወያኔ ግን አማራ ላደረገለት ቸርነት ከሻቢያና ከኦነግ ጋር በማበር አማራውን በበደኖ፣ ጉራ ፈርዳ፣ አርባጉጉና ሌሎችም አካባቢዎች በእጀ ዙር አሳረደ። ሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ በፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ አባዜ ተለክፈው በአማራው ላይ የፈፀሙት ግፍ ታሪክ ይቅር የማይለውና አሳፋሪው የጥላቻ ገድል ነው። አማራው ባለፉት ዘመናት ለአገሩና ለወገኑ ቆስሏል፣ ደምቷል፣ ህይወቱን ሁሉ መስዋዕት አድርጓል። ለዚህ ታላቅና አገር ወዳድ ህዝብ የተበረከተለት ስጦታ ግን ስደት፣ መፈናቀል፣ እስርና ሞት ነው።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የነገሮች ሁኔታ ስላላማራቸው አማራው ተሰባስቦ ለህልውናው የሚታገልበትን ድርጅት መዐሕድን መሰረቱ። የመዐሕድ መፈጠር ያስደነገጠው ወያኔም እኒህን ታላቅና ብርቅዬ ምሁር በማስወገድ መዐሕድን አፈራረሰው። ዛሬ በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው የተጠናና የተደራጅ ዘር የማጥፋት እንቅስቃሴ እረፍት በነሳቸው የአማራ ልጆች መመከት ሲጀምር በአማራ ልጆች በሚፈጠሩት የአማራ ድርጅቶች ላይ የጥላቻ ሰይፍ ከውስጥም ከውጭም መመዘዝ ተጀመረ። 


ሞረሽ ወገኔ የለኮሰው እሳት፣ ቤተ አማራ ያቀጣጠለው የአማራ ብሔርተኝነት መንፈስ ምድሪቷን ሲያጥለቀልቅና አህብንም ከአዴኃን ጋር ከመዋሃዱ በፊት ባደረገው ሰፊ የማንቃት ስራ አማራን ከተኛበት ሲቀሰቅስና በኋላም ዳግማዊ መዐሕድ ተመስርቶ አማራነት በሰማይና በምድር ሲዘመር፣ የአማራ ተጋድሎ ሲቀጣጠል፣ ጠላቶቻችን የሚይዙትና የሚጨብጡት ሲጠፋ፣ የአማራ ምሁራን ግን እንደ ኤማሆስ መንገደኞች የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ሙሾ ያንጎራጉራሉ። 

በተለይ የፕሮፌሰር አስራት አማራነትን የመታደግ ህልም የነበረው ዳግማዊ መዐሕድ እንደገና በምጥ ሲወለድ ፀረ አማራነት ጫጫታው ጨመረ። የጥላቻ ጦሮች ከእየ አቅጣጫው መወርወር ጀመሩ። ሄኖክ የሺጥላ፣ ሙሉቀን ተስፋው፣ መንበሩ አያሌው፣ መለክ ሃራና ሌሎችም የአማራ ከዋክብቶች በብዕራቸው ለአማራ ዘብ ቆሙ፣ ደረታቸውን ለጥላቻ ጦር ሰጥተው አማራ ተነስ እያሉ የአማራን ትንሳኤ በምድሪቷ ላይ አስተጋቡ።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ቆሜያለው የሚለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የአማራን መደራጀትና ወደ ትግል መግባት በግልፅና በስውር ማጥላላት ጀመረ። የጀግኖችን ተጋድሎ የወያኔ ቡትቶ እያለበሰ አቅጣጫ ለማስቀየር ተውተረተረ። በ2008 ዓ• ም በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች አማካኝነት ፀረ ወያኔ ትግል ተቀጣጠለ። የአማራ ተጋድሎ የተባለውን የአማራ ህዝብ መስዋዕትነት አርበኞች ግንቦት ሰባት ለራሱ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍ ለመሰብሰብና የአማራን ህዝብ የማንነትና የህልውና ተጋድሎ አቅጣጫ ለማስቀየር ተሯሯጠ። የአማራ ህዝብ በደምና በአጥንቱ ባቆያት አገር ውስጥ ሆኖ፣ አማራን አግልሎ፣ አማራን አፍኖ፣ ስለ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት መስበክ "የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ" ዓይነት ነው ዛሬ ለአዲሱ የአማራ ትውልድ። አማራውን ከእርስቱ ያገለለ፣ አማራውን ከመብቱ ያጎደለ፣ አማራውን ከአጠቃላዩ አገራዊ ፓለቲካና የለውጥ ጉዞ ያራቀ ትግል የትም አይደርስም። የአገሬ ሰው ሲተርት "በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ" ይላል።


በመሆኑም ለዚች አገር ህልውና፣ ነፃነትና ኩራት የአንበሳውን ድርሻ ያበረከተውን የአማራን ህዝብ መብትና ማንነት ማክበር ለድርድር የሚቀርብ አጀንዳ አይደለም። የአማራ ህዝብ በሻቢያ፣ በወያኔና በኦነግ ተሸውዷል፣ ዳግም በግንቦት ሰባት ግን አይሸወድም። አብረን ታግለን ነፃ እንውጣ፣ አገራችንን ከጥፋት እንታደግ ከተባለ በመጀመሪያ የአማራን ህዝብ ማክበር፣ ድርጅቶቹን ማክበርና በእውነትና በፍቅር መኖርን ይጠይቃል። የአማራ ህዝብ ጠላቶች የፍትህ ጠላቶች ናቸው፣ የነፃነት ጠላቶች ናቸው፣ የታሪክ ጠላቶች ናቸው፣ የእውነት ጠላቶች ናቸው። አሁን ወደ ፊት ለመጓዝና ከፊታችን ያሉትን መሰናክሎች በድል ለመወጣት አጠቃላዩ ፓለቲካችንና የአማራ ምሁራን የተንሸዋረረ እይታ ፓለቲካዊ ፈውስ ያስፈልገዋል። ከውሸትና ከተራ የድብብቆሽ ጨዋታ ነፃ መውጣት ያስፈልጋል።

የአማራ ህዝብ ማንነቱ ህልውናውና የከፈለው አኩሪ ገድል እስካልተበረለት ድረስ ትናንትናም፣ ዛሬም ሆነ ወደ ፊት ለአንድነትና ለኢትዮጵያዊነት መንፈስ መጠናከር የሚዘመረው መዝሙር "ውዳሴ ከንቱ" ነው። የአማራ ምሁራን ድንዛዜ፣ የዘመናት እንቅልፍ፣ የአዙሪት ጉዞ፣ ትውልዱን የማስበላት ጅላጅል የአንድነት ጨዎታ ይብቃ። ከዚህ በኋላ አማራነትን ዘምሩ፣ አማራነትን ስበኩ፣ አማራነትን ከፍ አድርጉ፣ ለአማራነት ተጠሉ፣ ለአማራነት ተወገዙ፣ ለአማራነት ተሰደዱ፣ ለአማራነት ተነቀፉ፣ ለአማራነት ታገሉ፣ ለአማራነት ሙቱ። ይህ ሲሆን የእናንተ ህሌና ተፈወሷል ማለት ነው፣ ጤናማ ሁኗል ማለት ነው፣ ትክክለኛ ነገር ማሰብ ጀምሯል ማለት ነው።

አማራነት ዳግም ለድርድር አይቀርብም!!
አማራነት በአዲሱ የአማራ ትውልድ ከፍ ብሎ ይዘመራል!!
ድል ለገናናው የአማራ ህዝብ!!
ውድቀት ለዘመናት የአማራ ጠላቶች!!
Read more
አማራ ወዳጆችን ማብዛት፤ ባላንጣዎችንም መቀነስ የሚችለው በራሱ ጠንክሮ ሲወጣ ብቻ ነው!

(መርከቡ ዘለቀ) 

በወቅቱ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በአማራ ህዝብ ላይ እጣታቸውን የሚቀስሩ ቡድኖች ብዙ መሆናቸውን እየተመለከትን ነው። በእርግጥ ህወሓትና ግብረ አበሮቹ የሀገር ሀብት እስከ ዳር ደንበሯ እየዘረፉ ባለበት ዘመን ለሀገር ጠበቃ ሆኖ የተገኘ ሁሉ ጠላት ሊበዛበት የግድ ነው፤ የሚጠበቅም ነው። ከአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች (ህወሓት፤ ሻብዕያና ኦነግ) በተጨማሪ የዛሬዎቹ ግንቦት 7 እና ሀገራዊ ንቅናቂ ተብየው ቡድንም የአማራን ህዝብ የሚወክሉ ድርጅቶችን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማውገዝ ላይ ይገኛሉ።

አሁን ግን እጅግ እየገረመንና እየመረረን የመጣው ግንቦት 7 የተባለው ሳያፈራ የጨነገፈው የምውታን ስብስብ የሚፈጥረው የማያባራ ንትርክ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት የግንቦት7 ከአሳዳሪዎቹ የተሰጠውን የቤት ስራ ለመስራት ሲል ነው በአማራ ስም የተደራጁ ቡድኖችን በባላንጣነት የፈረጀው።

ስለእውነት ግን ግንቦት 7 ለምን በአማራ ስም የተደራጁ ቡድኖችን ያወግዛል? ለምን ጸረ-ኢትዮጵያና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የጠራ አቋም ከሌላቸው ቡድኖች ጋር አብሮ ለመስራት እየታተረ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይደፈርስ አቋም ካላቸው የአማራ ድርጅች ጋር መስማማት/አብሮ መስራት ተሳነው?

እኔ ግንቦት 7ን ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮፓጋንዳዎች አንፃር ስመለከተው ራሱን በራሱ እያጠፋ/እየገደለ (ስዊሳይድ እየፈጸመ) ያለ ድርጅት መሆኑን ነው። ይህ እሳቤ እውነት የሚሆነው ግን ግንበት 7ን እንደ ሀገራዊ ድርጅት አድርገን ከወሰድነው ነው። አሁን አሁን ግን ግንቦት 7 አገራዊ ድርጅት መሆኑ ቀርቶ ዘረኛና ጸረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሆኑን እያስመሰከረ ነው። ዘረኛነቱን ባወጣው የድርጅቱ ውስጠ ድንብ (ከአማረኛ በተጨማሪ ሌላ ቋንቋ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን የገለጸበት) በሚገባ ተገለጾ ይገኛል፤ ጸረ-ኢትዮጵያነቱም የሻዕቢያ ተላላኪ በመሆኑና ከሌሎች ጸረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር በጋራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚያደርገው አንቅስቃሴ ይገለጣል።

ግንቦት 7 የህወሓትን መንግስት ማስወገድ(በህልሙ) የሚፈልገው ስልጣን ከህወሓት ወደ ግንቦት 7 ሰዎች በማሸጋገር ሌላ ዘረኛና የጥፋት ሰርአት ለመመሥረት እንጅ ሥር ነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ በማምጣት ሁሉም ዜጎች እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር ለመፍጠር አይደለም። ለዚህም ነው የህወሓትን በቋንቋ ላይ የተዋቀር ፌደራሊዝም እንዲቀጥል የሚፈልገው፤ ለዚህ ነው በዘር ላይ የተዋቀሩ ቡድኖችን ሲቀላቀሉ የህወሓትን ዘራኛ እና አግላይ አስተዳደር የሚቃወሙ ቡድኖችን የሚኮንነው።

ግንቦት 7 በቋንቋ ላይ የተመሠረተውን የወያኔ ክልላዊ አስተዳደር እንዳለ እቀበላለሁ ከሚልባቸው ምክንያቶች አንዱ የግብረ አበሮቹን ፍላጎት ለማሟላት ሲሆን የእነርሱም ምኞት በህወሓት ዘርኛ መንግስት ከአማራ ህዝብ የነጠቁትን ሰፊ መሬት እንደያዙ በሂደት ለመሸሽ ነው። ነገር ግን በእውነት የግንቦት 7 ጥረቅሞች የፖለቲካ ሰዎች ናቸው ወይ? አስተማማኝ አጋሩን አውግዞ ከመሰናክሉ ጋር የሚዶልቱ፤ በአሜሪካ ውብ ሆቴሎች እየተንፈላሰሱ አረበኞች ነን እያሉ በአረበኛ ስም የሚቀልዱ፤ ስለ ኢትዮጵያ እንታገላለን እያሉ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ዘንድ የሚሸጎጥ/የሚወተፉ፤ ጦር ሜዳ ሳይውሉ ነውጡን የፈጠርነው እኛ ነን እያሉ ያለ ሀፍረት በአደባባይ የሚዋሹ፤ ውጤት በሚስገኝ ስራ ላይ ከማተኮር ይልቅ በየጊዜው የንትርክ መድረክ ያሚዘጋጁ፤ ስለ ኢትዮጵያ እንታገላለን እያሉ በጀግና ኢትዮጵያውያን ደም እና አጥንት ተለወሶ የተጻፈውን የኢትዮጵያ ታሪክ ኢሳት በተባለው ሚዲያቸው የሚያርክሱ ከሆነ ግንቦት 7 ጤና የጎደላቸው ሰዎች ስብስብ እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ግንቦት 7 የጤነኛ ሰዎች ስብስብ ቢሆን ኑሮ ጸረ-ኢትዮጵያ አቋሙን ለማራመድ እንኳ አካሄዱን ከአጋሮቹ ከወያኔ እና ከሻዕብያ ይማር ነበር። በአርግጥ ከኦነግ ሊማር አይችልም ምክንያቱም ኦነግም ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ አንድ ጥይት እንኳ ሳይተኩስ በለንደን ሆቴሎች እየተዝናና ኢትዮጵያን አናፈርሳለን የሚል መናኛ ድርጅት በመሆኑ። ኦነግ መፈክሩ ብቻ ሳይሆ የሚገርመው ህልሙን ለማሳካት የሚጠቀምበት ስልት/ ስተራቴጅም ከንቱ ነው። ስለ እውነት ግን አንድ ጥያቄ አለኝ።

ከዚህ ጸረ-አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያ ከሆነው ግንቦት 7 ድርጅት ጋር አሁንም አባል ሁነው የሚደክሙ የአማራ ተወላጆች ካሉ እነርሱም በእውነት አብደዋል ማለት ነው። እርግጥ ነው ከአንድ አመት በፊት ብዙዎቻችን ተሸውደን ነበር። ስለ ኢሳትና ግንቦት 7 በየቀኑ ወሬ/ዜና ሳንሰማ ከዋልን አንድ ትልቅ ነገር እንዳመለጠን ይሰማን ነበር፤ ስለ ግንቦት 7 ሲወራ የተስፋ ጭላንጭል ይታይን ነበር። የግንቦት 7ን ድብቅ አጀንዳ በብዕራቸው ለተፋለሙና ላጋለጡ ውድ ኢትዮጵያን ምስጋና ይግባቸውና አሁን በግንቦት 7 ላይ የነበረው ተሰፋና መልካም ስሜት በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ላይመለስ ሙቶ ተቀብሯል። የሚቀጥለው ሥራ ግንቦት 7 እንደ ህወሓት ስረ ሰዶ/ገንግኖ ሳያስቸግር በሁሉም መስክ መፋለምና ማጥፋት ነው።

 የአማራን ህዝብ ከጥፋት ለመታደግ ከእውነት እየሰሩ ላሉ ቡድኖች የማስተላልፈው መልክት የአማራ ህዝብ ብዙ ወዳጆች እንዲኖሩትና የባላንጣዎቹም ቁጥር እንዲቀንስ ከተፈለገ ብቸኛው አማራጭ መንገድ አማራ በራሱ ጠንክሮ መውጣት አለበት የሚል ነው። ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ማንም እየተነሳ የአማራን ህዝብ ሲያዋርድ፣ ሲዘርፍ፣ ሲያሳድድ፣ በግፍ ሲገድል፣ ደም እና አጥነቱን የገበረበትን ታሪካዊ መሬቱን ሲነጥቀው የኖረበት ብቸኛው ምክንያት አማራ ጠንክሮ ባለመውጣቱ/ባለመደራጀቱ እንደሆነ ሁላችንም የሚያስማማ አብይ ጉዳይ ሆኗል።

ለዚህም ነው ተልካሻው ግንቦት 7 እንኳ ሳይቅር ያለ ምንም ሀፍረትና ፍርሀት ከ30 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የአማራ ህዝብ እራስህን ከጥፋት ለመከላከል መደራጅት የለብህም እያለ እያፌዘ የሚገኘው። ይህ ትዕቢት ህወሓትና ሻዕቢያ ከሚያሳዩት ትዕቢትም በላይ ነው። ምክንያቱም ሁለቱ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላቶች የትዕቢታቸው ምንጨ ለረጅም ጊዜ ማንም ሳይነቃ በወታደራዊ ኃይል መዘጋጀታቸው ብቻ ነው። ግንቦት 7 ግን በአውላላ ሜዳ ላይ የሚጮህ ከንቱ ሲሆን ሌላውን ሊያጠቃ ይቅርና እራሱን ለመከላከል እንኳ የማይችል ቡድን ነው።

ለመሆኑ ግን ግንቦት 7 በየትኛው አቅሙና ህጋዊ ሰውነቱ ነው የሌሎችን የመደራጀት መብት ቻሪና ከልካይ የሆነው? ግንቦት 7 ውስጣዊ ማንነቱ ሻዕቢያና ወያኔ መሆኑ እየታወቀ ከግንቦት 7 ጋር አብሮ ለመስራት የሚመኝ የአማራ ድርጅትስ እንዴት ሊኖር ይችላል? የግንቦት 7ም ሆነ የሀገራዊ ንቅናቄው ኢለማ አማራና ኢትዮጵያ ናቸው ። ለዚህ ነው ግንቦት 7 በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ሁሉ በአማራና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የሚዘምተው።

ግንቦተ 7 አማራንና ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከሚጠቀሙባቸው ስልቶች አንዱ ሰርጸ ደሰታ እንደገለፀው “የወያኔ የክት ሰዎችን” በመጠቀም ነው። ለዚህም ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምን በሲያትል ስብሰባ ተገኝተው ያደርጉትን የወረደ ንግግር እንደምሳሌ መውስድ እንችላለን። ግን ስለ እውነት እንነጋገረ ከተባለ ፕሮፌሰሩ አሁን ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው የማታውቀው ቀውስ ውስጥ በገባችበት ወቅት ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ስለመተሳሰብና በጋራ ስለመስራት ነው መስበክ/መናገር ያለባቸው ወይስ ሊያግባቡ በማይችሉ ጉዳዮች ላይ? አጼ ቴዎድሮስ ያለ ጊዜያቸው የተፈጠሩ ታላቅ መሪ መሆናቸው እየታወቀ አፄ ቴዎድሮስ ከህዝቡ ጋር አልተግባቡም ነበር ማለት ከፕሮፌሰሩ የሚጠበቅ የወቅቱ ንግግር ነው ወይ?

ኢትዮጵያ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ከተውጣጡ ጀግና እና አረበኛ ልጆቿ ተከብራ የኖረች ሀገር መሆኗ እየታወቀ ጀግናው በላይ ዘለቀ ጎጃሜ ቢሆንም ማንነቱ ኦሮሞ ነው ማለት በእውነት እንኳስ የፕሮፌሰር ንግግር ሊሆን ቀርቶ ፌደል ያልቆጠረ ሰው እንኳ ሊናገረው ይገባል ወይ? ሰረጸ ደስታ ሰለ ኦረሞ ደጋግሞ እንደገለጸው አሮሞ እኮ የራሱ ጀግና አላጣም ነበር፤ ችግሩ ጀግኖቹን ሁሉ የነፍጠኛ ወዳጆች ናቸው ብሎ በመካዱ ባዶ እጅኑ መቅረቱ ነው ። እንበልና ጀግናው በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ነው ብለን ብንቀበላቸው ፕሮፌሰሩ ምን ይፈጠር ነው የሚሉን? አማራ ጀግና የለውም ለማለት ከሆነ ፈጽሞ አያስኬድም።

በእውንት አንድ ስሙን ለጊዜው የማላሰታወሰው ወንድሜ ስለ ፕሮፌሰሩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፈው ጽፍ ለጽሁፉ የሰጠው ርዕስ “መገለባበጥ እንደ—— መክሸፍ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን” የሚል ነበረ፤ እውነት ነው በጣም ከሽፈዋል ፕሮፌሰሩ። በነገራችን ላይ ስለ ኮሌኔል መንግስቱ ኃይለማሪያምና የወታደራዊ መንግስት የውድቅት መንስኤዎች በሚያትት መጽሃፍ ላይ እንዳነበብኩት መንግስቱ ኃይለማሪያም እጅግ ካዘነባቸው ምሁራን መካከል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምና ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ይገኙባቸውል። መንግሰቱ ኃይለማሪያም እንደሚለው ወያኔ 1983 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ በደረሰበት ወቅት ምሁራኑ ለኢትዮጵያ አዋጭ መንገዶችን ከማቅረብ ይልቅ ለወያኔ አስተዋፆ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸውን በማንሳት በወቅቱ እንዳዘኑባቸው አንብቢያለው።

ስለዚህ ግንቦት 7 የወያኔን የክፉ ቀን ልጆች ከየቦታው እየመዘዘ ለመጠቀም የሚያደርገው ትርፍ የማያስገኝ አካሄድ ውድቀቱን ከማፋጥን ውጭ ሌላ ትርፍ አያስገኝለትም፣ ስልቱ ተነቅቶበታል፣ የክት ሰዎችም እነማን እንደሆኑ እየታወቀ ነው።

ሌላው ላለፈው 40 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያን ለማፈረስ የሻዕብያና ወያኔ አሽከር ሆኖ ሌት ከቀን ሲሰራ የኖረውና አሁንም ከዚህ ነውረኛ ሰራው ያልታቀበው አቶ ሌንጮ ለታ በሲያትሉ ስበሰባ “የኢተዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል” ሲል የምጸት ንግግር እንዳደረገ አነበብን። ይገርማል! ስለ አቶ ሌንጮ ለታ ምንነት አቶ ሰርጸ ደስታ በሚያስደት ሁኔታ የገለጸው ስለሆነ መድገም አያስፈልገም። ዶ/ር ብረሀኑ ነጋም የአሻንጉሊቶችን ስብስብ (ሀገራዊ ንቅናቄ ተብየውን) ኢትዮጵያን የሚመጥን ድርጅት ነው በሚል ያደረገውን ንግግር እንዲሁ በድረ ገጽ አነበብን ። በእውነቱ ኢትዮጵያን የሚወክለውና የሚመጥነው ኢትዮጵያን ለማፈረስ ሲጥር የኖረውና አሁንም ኢትዮጵያ ብሎ መጥራት የሚጸፈው፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ ሲያይ የሚበረግገው የሌንጮ ለታ ድርጅትና የሻዕቢያ ተላላኪ የሆነው የግንት 7 ድርጅት በአንድ ላይ የመሠረቱት የጥፋት ቡድን እንዴት ነው ኢትዮጵን የሚመጥነው? ምን አልባትም በውስጥ ወይራ ንግግር ደ/ሩ ማለት የፈለገው ኢትዮጵያን ለማፍረስ አቅም ያለው ጸረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሥረተናል ለማለት ሊሆን ይችላል። ይኸኛውም ሀሳብ ቢሆን ሊሳካላቸው የሚችል አይደለም።

ኢትዮጵያ እጅግ የምትገርም ሀገር ናተ። በክፉ ቀን ከጎኗ ተሰልፈው መሰዋት የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ ችግር በገጠማት ቁጥር ከቅጥረኞች ጋር በማበር ያለማንም ተከላካይ የቡድን ጥቅማቸውን ለማሳካት የሚሮጡ ብዙ ናቸው።በተለይ በአሁኑ ወቅት ከዘረኛው ህወሓት ትግሬ በተጨማሪ ኦነግና ግብረ አበሮቹ አሁን እየሰሩት ያለው የቆሸሸና ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት ይህንኑ ነው። ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የሁሉም ጠላት በሆነው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ማንሳት ሲገባቸው እንገነጠላልን፤ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት እንዲሁም በባንዲራዋ ላይ መደራደር ይገባናል ይሉናል። ሀገረ ውስጥ ያለው የህወሓት ቡችላ ኦህዴድም በአዲስ አበባ ላይ እየሰራ የሚገኘው ሴራ ከኦነግ ጋር በመተባበር ነው። ለመሆኑ ግን ከሃዲውና ዘራፊው ወያኔ ያለማንም ተከላካይ የሚተላልፈው የክህደት ውሳኔ ተቀብሎ የሚኖር ህዝብ ሊኖረ እንደማይችል እንዴት ኦህዴዶች/ኦነጎች መረዳት ተሳናቸው? ኦህዴዶች እና ኦነጎች የሸዋ ኦሮሞ ጀግኖችን እያዋረዱ ለምን በአዲስ አበባ ላይ መስገብገብ አበዙ? የሸዋ ጀግኖችን ከጠሉ ጀግኖቹ ከሌላው ወገናቸው ጋር ተባብረው የመሠረቷትን ከተማ ለምን ይፈልጓታል? ግለሰቡን ከጠሉ ንብረቱን መመኝት አያስኬድም። የኦህዴዶችና ኦነጎች ዘዴ ግልጽ ነው። የገቢያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው የወቅቱን የፖለቲካ ቀውስና የአማራን አለመጠናከር ተጠቅመው አዲስ አበባን በግርግር ለመንጠቅ ነው። የወያኔ ስልትም እንዲሁ ግልጽ ነው። የአማራን የትግል አቅጣጫ ማስቀየርና ጠላቱንም ማብዛት ነው።

ወደ ማጠቃለያ መልክቴ ስመለስ በአማራ ስም ተደራጅታችሁ አማራን ከጨርሶ መጥፋት ለመከላከል እየተንቀሳቀሳችሁ የምትገኙ ቡድኖች ሁሉ መረዳት የሚገባችሁ አብይ ጉዳይ አማራ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ የገባ መሆኑን ተርድታችሁ ይህን ከፍተኛ ፈተና በአሸናፊነት ለማለፍ በአንድነትና በጽናት በመቆም ቆራጥ እና ሀገር ወዳድ ወገናችሁን ማደራጀትና ወደ ትግል መምራት ይኖርባችኋል። እያንዳንዱ አማራም በሀወሓት ትግሬና በግበረ አበሮቹ የተገፈፈውን ነፃነቱን ለማስመለስ የትኛውንም አይነት መሰዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን ይኖርበታል። ልጆቻችን በኢትዮጵያ እንደዜጋ ተከብረውና መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከፈለግን እኛ መሰዋት ልንከፍል የግድ ነው። ማለፋችን ላይቀር ስደትንና ውርደትን ልጆቻችን አውርሰን ማለፍ የለብንም።

ድል ለኢትዮጵያ!
Read more