Open top menu
June 28, 2017

ኃያል ሰው
ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓ.ም
ከአዲሲቷ የአማራ ምድር
ፈለገ ጊዮን
ባህር ዳር


የ1960ዎቹ የአማራ ትውልድ በሰሩት ታሪካዊ ስህተት ዛሬ የአማራ ህዝብ ለሚገኝበት ዘርፈ ብዙ ችግር ዋና ምክንያት ሆኖ ይገኛል። ዘውዳዊውን ስርዓት በጭፍንና በቂ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ እንዲወገድ የአማራ ልጆች እንደ ዋለልኝ ያሉትያሉት የተጫወቱት ሚና በአማራነት ላይ የተከፈተው የመጀመሪያው ታሪካዊ ጠላትነት ነበር። የዘውዳዊው ስርዓት በአማራ ልጆች አጃቢነት መወገድ ለአማራ ጠላቶች ሰፊ በርን ከፈተላቸው። ሶማሌ በምስራቅ፣ ሻቢያና ወያኔ በሰሜን፣ ሱዳን በምዕራብ በአገራችን ላይ ፀረ አማራና ኢትዮጵያዊ ትግል አቀጣጠሉ። የዚያ ትውልድ ታሪካዊ ስህተት በተለይም የአማራ ምሁራን ማንቀላፋት ለፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ መፈጠር ጉልህ ሚና ነበረው። በቀይና ነጭ ሽብር ሰበብ አገር ወዳድ የአማራ ልጆች እየታደኑ ተረሸኑ፣ ከአገር ተሰደዱ፣ ወደ እስር ተወረወሩ። በአማራ ማንቀላፋትና አለመንቃት በኢትዮጵያ ትቅደም ካባ ስር "አማራ ይውደም" የሚል የትግል ስልት ውስጥ ለውስጥ ተቀጣጠለ። ሻቢያና ወያኔ የደርግን ቡትቶ ለብሰው በገጠርና በከተማ አማራን የማፈንና የመግደል ዘመቻ አፋፋሙ።


እነዚያ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አንድነትና ነፃነት የተሟገቱ ብርቅዬ ንጉስ በሆያ ሆዬ ጩኸት ወደ መቃብር ተሸኙ። የአፄ ኃይለ ስላሴ በግፍ ከስልጣን መውረድና የ60 ሚኒስትሮች በአደባባይ መረሸን የአማራ ውድቀት የማንቂያ ደወል ነበር። ሆኖም ግን አማራ ከመንቃት ይልቅ በየዋህነት እራሱን በማጥቃት ከፀረ አማራ ኃይሎች ጋር ተሰለፈ። ህወኃት በ1967 ዓ• ም ሲፈጠር ዋናው ዓላማ አማራን ማጥፋትና ኢትዮጵያን ማፈራረስ ነበር። ወያኔም በበኩሉ ከሻቢያ በተሰጠው ተልኮ መሰረት የፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ትግሉን ለ17 ዓመታት አቀጣጠለው። ያኔም በተመሳሳይ የአማራ ልጆች ከአማራ ጠላቶች ጋር በማበር አብረው ታግለውና መንገድ መርተው ወያኔን ለዙፋን አበቁት።

ወያኔ ግን አማራ ላደረገለት ቸርነት ከሻቢያና ከኦነግ ጋር በማበር አማራውን በበደኖ፣ ጉራ ፈርዳ፣ አርባጉጉና ሌሎችም አካባቢዎች በእጀ ዙር አሳረደ። ሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ በፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ አባዜ ተለክፈው በአማራው ላይ የፈፀሙት ግፍ ታሪክ ይቅር የማይለውና አሳፋሪው የጥላቻ ገድል ነው። አማራው ባለፉት ዘመናት ለአገሩና ለወገኑ ቆስሏል፣ ደምቷል፣ ህይወቱን ሁሉ መስዋዕት አድርጓል። ለዚህ ታላቅና አገር ወዳድ ህዝብ የተበረከተለት ስጦታ ግን ስደት፣ መፈናቀል፣ እስርና ሞት ነው።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የነገሮች ሁኔታ ስላላማራቸው አማራው ተሰባስቦ ለህልውናው የሚታገልበትን ድርጅት መዐሕድን መሰረቱ። የመዐሕድ መፈጠር ያስደነገጠው ወያኔም እኒህን ታላቅና ብርቅዬ ምሁር በማስወገድ መዐሕድን አፈራረሰው። ዛሬ በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው የተጠናና የተደራጅ ዘር የማጥፋት እንቅስቃሴ እረፍት በነሳቸው የአማራ ልጆች መመከት ሲጀምር በአማራ ልጆች በሚፈጠሩት የአማራ ድርጅቶች ላይ የጥላቻ ሰይፍ ከውስጥም ከውጭም መመዘዝ ተጀመረ። 


ሞረሽ ወገኔ የለኮሰው እሳት፣ ቤተ አማራ ያቀጣጠለው የአማራ ብሔርተኝነት መንፈስ ምድሪቷን ሲያጥለቀልቅና አህብንም ከአዴኃን ጋር ከመዋሃዱ በፊት ባደረገው ሰፊ የማንቃት ስራ አማራን ከተኛበት ሲቀሰቅስና በኋላም ዳግማዊ መዐሕድ ተመስርቶ አማራነት በሰማይና በምድር ሲዘመር፣ የአማራ ተጋድሎ ሲቀጣጠል፣ ጠላቶቻችን የሚይዙትና የሚጨብጡት ሲጠፋ፣ የአማራ ምሁራን ግን እንደ ኤማሆስ መንገደኞች የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ሙሾ ያንጎራጉራሉ። 

በተለይ የፕሮፌሰር አስራት አማራነትን የመታደግ ህልም የነበረው ዳግማዊ መዐሕድ እንደገና በምጥ ሲወለድ ፀረ አማራነት ጫጫታው ጨመረ። የጥላቻ ጦሮች ከእየ አቅጣጫው መወርወር ጀመሩ። ሄኖክ የሺጥላ፣ ሙሉቀን ተስፋው፣ መንበሩ አያሌው፣ መለክ ሃራና ሌሎችም የአማራ ከዋክብቶች በብዕራቸው ለአማራ ዘብ ቆሙ፣ ደረታቸውን ለጥላቻ ጦር ሰጥተው አማራ ተነስ እያሉ የአማራን ትንሳኤ በምድሪቷ ላይ አስተጋቡ።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ቆሜያለው የሚለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የአማራን መደራጀትና ወደ ትግል መግባት በግልፅና በስውር ማጥላላት ጀመረ። የጀግኖችን ተጋድሎ የወያኔ ቡትቶ እያለበሰ አቅጣጫ ለማስቀየር ተውተረተረ። በ2008 ዓ• ም በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች አማካኝነት ፀረ ወያኔ ትግል ተቀጣጠለ። የአማራ ተጋድሎ የተባለውን የአማራ ህዝብ መስዋዕትነት አርበኞች ግንቦት ሰባት ለራሱ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍ ለመሰብሰብና የአማራን ህዝብ የማንነትና የህልውና ተጋድሎ አቅጣጫ ለማስቀየር ተሯሯጠ። የአማራ ህዝብ በደምና በአጥንቱ ባቆያት አገር ውስጥ ሆኖ፣ አማራን አግልሎ፣ አማራን አፍኖ፣ ስለ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት መስበክ "የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ" ዓይነት ነው ዛሬ ለአዲሱ የአማራ ትውልድ። አማራውን ከእርስቱ ያገለለ፣ አማራውን ከመብቱ ያጎደለ፣ አማራውን ከአጠቃላዩ አገራዊ ፓለቲካና የለውጥ ጉዞ ያራቀ ትግል የትም አይደርስም። የአገሬ ሰው ሲተርት "በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ" ይላል።


በመሆኑም ለዚች አገር ህልውና፣ ነፃነትና ኩራት የአንበሳውን ድርሻ ያበረከተውን የአማራን ህዝብ መብትና ማንነት ማክበር ለድርድር የሚቀርብ አጀንዳ አይደለም። የአማራ ህዝብ በሻቢያ፣ በወያኔና በኦነግ ተሸውዷል፣ ዳግም በግንቦት ሰባት ግን አይሸወድም። አብረን ታግለን ነፃ እንውጣ፣ አገራችንን ከጥፋት እንታደግ ከተባለ በመጀመሪያ የአማራን ህዝብ ማክበር፣ ድርጅቶቹን ማክበርና በእውነትና በፍቅር መኖርን ይጠይቃል። የአማራ ህዝብ ጠላቶች የፍትህ ጠላቶች ናቸው፣ የነፃነት ጠላቶች ናቸው፣ የታሪክ ጠላቶች ናቸው፣ የእውነት ጠላቶች ናቸው። አሁን ወደ ፊት ለመጓዝና ከፊታችን ያሉትን መሰናክሎች በድል ለመወጣት አጠቃላዩ ፓለቲካችንና የአማራ ምሁራን የተንሸዋረረ እይታ ፓለቲካዊ ፈውስ ያስፈልገዋል። ከውሸትና ከተራ የድብብቆሽ ጨዋታ ነፃ መውጣት ያስፈልጋል።

የአማራ ህዝብ ማንነቱ ህልውናውና የከፈለው አኩሪ ገድል እስካልተበረለት ድረስ ትናንትናም፣ ዛሬም ሆነ ወደ ፊት ለአንድነትና ለኢትዮጵያዊነት መንፈስ መጠናከር የሚዘመረው መዝሙር "ውዳሴ ከንቱ" ነው። የአማራ ምሁራን ድንዛዜ፣ የዘመናት እንቅልፍ፣ የአዙሪት ጉዞ፣ ትውልዱን የማስበላት ጅላጅል የአንድነት ጨዎታ ይብቃ። ከዚህ በኋላ አማራነትን ዘምሩ፣ አማራነትን ስበኩ፣ አማራነትን ከፍ አድርጉ፣ ለአማራነት ተጠሉ፣ ለአማራነት ተወገዙ፣ ለአማራነት ተሰደዱ፣ ለአማራነት ተነቀፉ፣ ለአማራነት ታገሉ፣ ለአማራነት ሙቱ። ይህ ሲሆን የእናንተ ህሌና ተፈወሷል ማለት ነው፣ ጤናማ ሁኗል ማለት ነው፣ ትክክለኛ ነገር ማሰብ ጀምሯል ማለት ነው።

አማራነት ዳግም ለድርድር አይቀርብም!!
አማራነት በአዲሱ የአማራ ትውልድ ከፍ ብሎ ይዘመራል!!
ድል ለገናናው የአማራ ህዝብ!!
ውድቀት ለዘመናት የአማራ ጠላቶች!!
Tagged
Different Themes
Written by Lovely

Aenean quis feugiat elit. Quisque ultricies sollicitudin ante ut venenatis. Nulla dapibus placerat faucibus. Aenean quis leo non neque ultrices scelerisque. Nullam nec vulputate velit. Etiam fermentum turpis at magna tristique interdum.

0 comments